የዘመናችን ሐዋርያዊ “ሹመት” በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ሲቃኝ

የዘመናችን ሐዋርያዊ ሹመት” በመጽሐፍ ቅዱ አስተምህሮ ቃኝ

በተካልኝ ዱጉማ

Duguma@gmail.com

ከጓደኞቼ ጋር ስናወጋ፣ በድንገት አንድ ዜና መሰል ነገር በጆሮዬ ጥልቅ አለ። ዜናውም በከተማችን በጣም የታወቁ አንድ መጋቢ ሐዋርያ ተብለው “ሊሾሙ” የመሆኑ ጉዳይ ነበር (አሁን ግን “ሐዋርያ” ተብለው ተይመዋል)። ይህን ሐሳብ በአእምሮዮ ሳውጠነጥን “በሆዶስ” መጽሔት በዚሁ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኰረ ጽሑፍ ቀረበ። የመጋቢው ሐዋርያ ሆኖ ለመሾም መታሰብ እና የጽሑፉ ይዘት ተቃራኒ ስለሆነ፣ በእኔ ብቻ ሳይሆን ይህንን ዜና በሰሙ ሕዝበ ክርስትያን አእምሮ ውስጥ ጥያቄ መፍጠሩ የማይቀር ነው። ምክንያቱም የአዲስ ኪዳን ሐዋርያነት ከሙሉ ባለሥልጣንነት ጋር የተቈራኘ በመሆኑ ነው። ከዚህ በተጨማሪ “ካቦድ” በተባለ መጽሔት ላይ እስክንድር ታደሰ የተባሉ ሰው “በቅድሚያ ሐዋርያነት እንደ []ላሴ፣ የክርስቶስ ማዕከልነት፣ የቃሉን ክቡርነትና የመሳሰሉ የገዘፉ የአስተምህሮ ቁም ነገሮችን ያህል የሚመዘን ሙሉ ጊዜ ሰጥቶ ተቋም አቋቁሞ መሞገትን የሚጠይቅ ጉዳይ አለመሆኑን ማሰብ ተገቢ ይመስለናል” [1] በማለት የመሰላቸውን አስተያት በመስጠት ነገሩን ቸል ብለን እንድናልፈው መክረውናል። ይሁንና ይህንን ሐዋርያት በዘመናችን አሉ ወይስ የሉም የሚለውን ሐሳብ ለመሞገት የተቋቋመ ተቋም እስከ አሁን ድረስ በአገራችን ባለመኖሩ ምን ለማለት እንደፈለጉ ግልጽ አልሆነልኝም። “. . . እና . . . ሲወስድ እያሳሳቀ ነው” እንደሚለው አገረኛ ብሕል እኝሁ ሰው “ር[]ሱ . . . የመገናኛ ብዙሃኖችን አድማቂ ር[]ስ ብቻ ከመሆን ያለፈ አሳሳቢነት የለውም” [2] ይላሉ። በእርግጥ ይህ እውነት ነውን? ስለዚህ ነገር የሚኖረን አስተምህሮ ምንም ዐይነት ችግር ከሌለበት ጳውሎስ በመልእክቶቹ ውስጥ ሐዋርያ እንደ ሆነ ለምን መሞገት አስፈለገው? ሐዋርያነቱን ለተቃወሙት ሰዎች ሲሞግት እና አስረግጦ ምላሽ ሲሰጥ ወደ ገላቲያ፣ ሮሜ እንዲሁም 1ኛ እና 2ኛ ቆሮንቶስ ሰዎች በተላኩ መልእክቶቹ ውስጥ እንመለከታለን። ነገሩ “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት” መሆኑ አይደል? ይህ ሰዎቻችን ወዴት እየሄዱ ነው አያሰኝም? በእኔ ውስጥ እንደ ሰዎች ሁሉ ሁኔታው ጥያቄን ስለፈጠረ፣ ምላሽ ወደማገኝበት መጽሐፍ ቅዱስ ለመሄድ መረጥሁ።

ከጥናቴም በኋላ ይህንን ጽሑፍ ልጽፍ ስነሣ ብዙ ሐሳቦች በአእምሮዬ ውስጥ ይላወሱብኝ ነበር። የዚህ ጽሑፍ ዐላማ ምን መሆን አለበት? በዚህ ጽሑፍ እኔ ምን አዲስ ነገር መጨመር እችላለሁ? በመጽሔት ለተጻፉት ጽሑፎች ብቻ አዎንታዊም ይሁን አሉታዊ ምላሽ ልስጥ ወይስ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሐዋርያት የሚያስተምረውን በስፋት በመዳሰስ፣ እግረ መንገዴን በመጽሔት ላይ ለቀረቡ ሐሳቦች መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ አዎንታዊም ይሁን አሉታዊ ምላሽን በመስጠት ለሕዝበ ክርስትያኑ በዚህ ርእሰ ጉዳይ ዙርያ በቂ ዕውቀት የሚያስጨብጥ ነገር ላቅርብ? በአእምሮዬ ውስጥ ለሚመላለሱብኝ ጥያቄዎች ምላሽን አገኝ ዘንድ የመረጥሁት የመጨረሻውን ሐሳብ ይኸውም፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሐዋርያት የሚያስተምረውን ትምህርት በቅርበት በመመርመር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሽን መስጠት የሚለውን መንገድ ነው። የዚህ ጽሑፍ ዐላማም በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮን የዘመናችንን “ሐዋርያዊ ሹመት” መገምገም ይሆናል። በጥናቴም ያገኘሁትንም ምላሽ ለእናንተ እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሐዋርያ ተብሎ የተተረጎመው (avpo,stoloj) የሚለው የግሪኩ ቃል የተለያዩ ትርጓሜዎችን ለማመልከት ውሏል። avpo,stoloj የሚለው ቃል የስም ስዋሰዋዊ ይዘት ስኖረው፤ ግሣዊ ይዘቱ ደግሞ ἀποστέλλω ነው። ምንም እንኳ አንዳንድ ሰዎች ሐዋርያት ተብሎ የተተረጎመው ቃል avpo,stoloj ግሣዊ ይዘት እንዳለው አድርገው ለመከራከርያ ነጥባቸው ቢያነሱትም avpo,stoloj ግን ሁል ግዜም ስማዊ ይዘት ያለው ነው፤ ጸሓፍቱ ቃሉን ἀποστέλλω በሚለው መልኩ ግን ከተጠቀሙበት ግን የሚያመለክተው ግሥን ይሆናል። በስም ስዋሰዋዊ ቀመር የተቀመጠው avpo,stoloj በስልጣን የተላኩ ሰዎችን የሚያመለክት እንጂ መልዕክታቸውን ወይም መላካቸው የሚያመለክት አይደለም። ምንም እንኳ የስልጣናቸው ምንጭ ክርስቶስም ወይም ቤተክርስቲያን አልያም ሌላ ልሆን ቢችልም "ይህ ቃል (በስማዊ ቀመሩ) መላክ ወይም መልዕክት የሚል ትርጓሜ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ኖሮት አያውቅም፤ ይህ ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ ዘወትር የሚያመለክተው በሙሉ ስልጣን የተላኩ ሰዎችን ነው” [3] የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱሳችንም ሐዋርያ ብሎ የተረጎመው avpo,stoloj እንጂ ἀποστέλλω እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባል። ስለዚህም የቃሉን ፍች በትክክል ለመገንዘብ እንዲረዳን ሐዋርያ የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ ጸሓፍቱ ያስቀመጡአቸውን አማረጭ ፍችዎች በጥቅቱ እንመልከት፦

1. የኢየሱስን ተልእኮ ለመፈጸም በኢየሱስ ክርስቶስ የተጠሩ ዐሥራ ሁለቱን ሐዋርያትን ያመለከታል (ማቴ 10÷2)። በዚህ ክፍል ቁጥራቸው ዐሥራ ሁለት መሆኑ፣ ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤልን ነገዶች እንድናስታውስ ያስገድደናል (ማቴ 19÷28፤ማር 3÷14-15 ሉቃ 22÷14፣ 29-30) ይህ ብቻ ሳይሆን ይህ ቁጥር የኢየሱስን መሲሕነት በተቀበሉ ሰዎች የተዋቀረ መሆኑን በማሳየት የአዲስቷን እስራኤል ምንነት ያሳያል። እነኝህ ለወደ ፊት በእስራኤል ነገድ ላይ እንደሚፈርዱ ተነግሮላቸዋል። ይህ በሌላ አባባል በኢየሱስ መሲሕነት ያላመኑት እስራኤላውያን ከመጭው የእግዚአብሔር መንግሥት ሲወገዱ፣ ያመኑት ግን የእግዚአብሔር መንግስት ተካፋዮች ይሆናሉ ማለት ነው።

2. ሌላኛው ዐሥራ ሁለቱን እና ሌሎቹን ያቀፈ ሲሆን በመጠኑም ሰፋ ይላል። ይህ ከሞት የተነሣውን ኢየሱስ ክርስቶስን የተመለከቱትን እና ከእርሱ በቀጥታ ተልእኮን የተቀበሉትን የሚያመለክት ነው (1ቆር 15÷7 9÷1)፤ እንዲሁም አስተምህሮአቸው የቤተ ክርስቲያን መሠረት የሆኑ ሰዎች ናቸው (ኤፌ 2÷20 3÷5 4÷11)። ምንም እንኳ ሉቃስ ከሐዋ 14÷4፡ 14 ውጭ ሐዋርያ የሚለውን ስያሜ ለዐሥራ ሁለቱ ብቻ የተጠቀመ ቢሆንም፣ ጳውሎስ ግን አዳዲስ ቤተ ክርስቲያናትን የተከሉትን ምስክርነታቸውንም ባቋቋሟቸው አብያተ ክርስቲያናት የሚያረጋግጡትን ሰዎች ሐዋርያ በማለት ጠርቷቸዋል (1ቆሮ 9÷2)። እነዚህ ሐዋርያት ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ወገን ያልሆኑ ነገር ግን ከዐሥራ ሁለቱ ጋር እኩል የክርስቶስ ሐዋርያት ተብለው የሚጠሩ ናቸው።

3. ሰፋ ባለ መልኩ ይህ ቃል በቤተ ክርስቲያን የተወከሉ/የተላኩ ሰዎችን ለማመልከት የአዲስ ኪዳን ጸሓፍት ተጠቅመውበት እንደ ነበረ እንመለከታለን (2ቆሮ 8÷ 16-24 ፣ 23 ፊል 2÷25)። እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያት (avpo,stoloi evkklhsiw/n) በመባል ይታወቃሉ። ማለትም ቤተ ክርስቲያን እንደራሴዎቿ ይሆኑ ዘንድ የወከለቻቸው ሰዎች ናቸው።

4. ሐዋርያ የሚለው መጠሪያ ለኢየሱስ ክርስቶስ ውሏል (ዕብ 3÷1)።

5. በመጨረሻው የጳውሎስ ተቀናቃኞች ሐሰተኛ ሐዋርያት በማለት ይጠራቸዋል (2ቆሮ 11÷ 13)።

ከላይ ከተዘረዘሩት መካከል ከዚህ ጽሑፍ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለው በቁጥር አንድ እና ሁለት ላይ የተጠቀሱት ፍችዎች ናቸው። በተራ ቁጥር ሁለት ላይ ያለው የሐዋርያነት መጠርያ ፍች የሐዋርያትን ቁጥር ከዐሥራ ሁለት በላይ በማድረጉ ምክንያት በዘመናችን ሰዎች የሐዋርያነት ጸጋ አለ ወደ ማለት አድርሷቸዋል።በዚህ ዘመን ሐዋርያት በእርግጥ አሉ[4] በማለት ደምድመዋል። እኔ ግን ቆይ ወደ ድምዳሜ ለመድረስ የምን መቸኮል ባይ ነኝየቸኮለች አፍሳ ለቀመችነውና። ሐዋርያት በዘመናችን አሉ ያሉት የአንድ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ፕረንስፓልምክንያታቸውን ሲገልጹክርስቶስ ሐዋርያትን የሰየመበት መነሻ ምክንያት ስያሜና ለታ ነው፤ ወይስ አገልግሎት? መነሻው ስያሜነት ሳይሆን አገልግሎትና []ደራ እስከ ሆነ ድረስ፣ ይህ የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ እስኪደመደም የሚቀጥል በመሆኑ ሐዋርያነት ይቀጥላል የሚለው ከፍታቴም (Exegesis) ከአመክንዮም (Reason) አንጻር አሳማኝ ነው።ብለዋል።[5] በእርግጥ እርሳቸው ያሉት ልክ ነውን? በጭራሽ አይደለም። የወንድማችን ሀሳብ እስከገባኝ ድረስ ሐዋርያነት አገልግሎት በመሆኑ ምክንያት እስከ ዓለም ፍጻሜ መቀጠል አለበት ይመስላል። ይህ አገልግሎትስ ቢሆን ለምን ይቀጥላል? የሚል ጥያቄ እንድጠይቅ ያስገድደኛል። ምክንያቱም ሐዋርያ ተብሎ በአማሪኛ መጽሐፍ ቅዱስ የተተረጎመው ቃል የሚያመለክተው አገልግሎትን ሳይሆን አገልጋዩን ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሐዋርያተ ተብሎ የተተረጎመው ቃል በግሣዊ ይዘት ሲመጣ ግን አገልግሎትን ያመለክታል። ምንም እንኳ ሐዋርያቱ ሐዋርያ የመሆናቸው ምክንያት ለአገልግሎት ቢሆንም ይህ የተሰጣቸው አገልግሎት ለምን ወንድማችን “የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ እስኪደመደም የሚቀጥል” ነው ያሉበት ምክንያቱ ግልጽ አይደለም። በእርግጥ ወድማችን ለማሳመኛነት ሊያነሷቸው የሚችሉ ጥቅሶች ይኖሩ ይሆናል። ምንም እንኳ እነዚህ ክፍሎች እሳቸው የተከተሉትንይነት ትርጓሜ ባይኖራቸውም። ለምሳሌ ያህል ኤፌ 4÷11-13 እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ አንዳንዶቹ ነቢያት፥ አንዳንዶቹ የወንጌል ሰባኪዎች፥ አንዳንዶቹ የምእመናን እረኞች፥ አንዳንዶቹ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ስጦታዎችን ሰጣቸው። ይህንንም ያደረገው የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እንድትታነጽ፥ ምእመናንን ለክርስቲያናዊ አገልግሎት ለማዘጋጀት ነው። እንዲሁም የእግዚአብሔርን ልጅ በማወቅ በእምነት ወደሚገኘው አንድነት ደርሰን፥ ክርስቶስ ፍጹምና ሙሉ እንደሆነው ዐይነት እኛም ሙሉ ሰው እንድንሆን ነው። (የ1980 ትርጉም) ይህ በእርግጥ ለቤተ ክርስቲያን የተሰጡ ሰዎችን ያመለክታል ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን እስካለች ድረስ እነዚህ ስጦታዎች ሊኖሩ ይገባቸዋል በማለት የሚሞግቱ ሰዎች መነሻቸው በ1954 ትርጉም ላይ “ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።” የሚለው ጥቅስ ሲሆን “እስክንደርስ ድረስ” የሚለው ቃል ጊዜ አመልካች ቃል እንደሆነ በእማኝነት ያነሳሉ። ነገር ግን የዚህ ቃል ትክክለኛ ትርጓሜ በUBS ከተዘጋጀው የግሪክ መጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተቀራራቢ ትርጓሜ ያለው የ1980 ትርጉም እንደሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን[6] ይስማማሉ። ቃሉም ሊተረጐም የሚገባው “ደርሰን” በሚል የመጨረሻ ግብን በሚያሳይ ቃል ነው። ይህ ከሆነ የሐዋርያት አገልግሎት ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮዋን እስክትፈጽም ድረስ መቀጠል አለበት የሚለው የጊዜ አመልካች ቃልን መሠረት ያደረገው የወንድማችን አመክኖዎ ምክንያት የሚጐለው እና ተቀባይነት የማይኖረው ይሆናል። ምክንያቱም አመክንዮው መሠረት ያደረገው የተዛባ ፍታቴ ላይ በመሆኑ ነው።

በተጨማሪም በሥነ አፈታት መርሕ መሠረት አንድ ቃል ወይም ዐረፍተ ነገር ከተጻፈበት ዐውድ ውጭ ትርጓሜውን ማግኘት አይቻልም የሚለውን መርሕ ልብ ልንል ይገባል። ስለዚህ ሙሉውን የኤፌሶን መልእክት በምናነብበት ጊዜ ኤፌ 2÷20 በሐዋርያትና በነብያትም መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማእዘኑም ራስ ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሕንጻው በሙሉ በእርሱ ተገጣጥሞ የጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ለመሆን ያድጋልይላል። ወንድማችን ቤተ ክርስቲያን በየጊዜው/ በየዘመናቱ በሐዋርያት እና በነብያት መሠረት ላይ ትታነጻለች እንደማይሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ ምክንያቱም የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አንድ ጊዜ በምድር ላይ ተመሥርታለችና:: [7] ነገር ግን በሐዋርያት እና በነቢያት መሠረት ላይ የተገነባችው የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ እየሰፋች እና እያደገች ትሄዳለች። እንዲሁም ኤፌ 3÷5 “ ይህም ምሥጢር በእግዚአብሔር መንፈስ ለቅዱሳን ሐዋርያቱና ነቢያቱ አሁን እንደ ተገለጠው ዐይነት ባለፉት ዘመናት ለነበሩት ሰዎች አልተገለጠም።ይላል። ይህ ደግሞ እግዚአብሔር ለሐዋርያት እና ለነቢያት እንዴት አሕዛብ የእግዚአብሔር መንግሥት ተካፋይ እንደ ሆኑ የሚያሳየውን ምሥጢር እንደገለጠላቸው እንመለከታል። ከእነዚህ ክፍሎች እንደምንረዳው ኤፌ 4÷11 ላይ ያለው ሐዋርያ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበትን አስተምህሮ እንዲያስተምሩ ምሥጢር የተገለጠላቸው በክርስቶስ በራሱ የተሾሙ ሰዎችን ነው። ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያት ስለ ክርስቶስ ባስተማሩት አስተምህሮ ላይ የተመሠረተች ነችና። 1ቆሮ 3÷9-11 “እኛ ለእግዚአብሔር አብረን የምንሠራ አገልጋዮች ነን፤ እናንተም የእግዚአብሔር እርሻና የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ። እግዚአብሔር በሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልኅ ግንበኛ መሠረትን ጣልኩ፤ ሌላውም እኔ በጣልኩት መሠረት ላይ ይገነባል፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በዚያ ላይ እንዴት እንደሚገነባ መጠንቀቅ አለበት። አንድ ጊዜ ከተመሠረተው መሠረት በቀር ማንም ሌላ መሠረት መጣል አይችልም፤ ይህም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።በእነዚህ ምክንያት ምንም እንኳ ሐዋርያነት አገልግሎት ቢሆንም በየዘመናቱ የሚጣል መሠረት የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ስለሌላት ወንድማችንሐዋርያነት ይቀጥላል የሚለው ከፍታቴም (Exegesis) ከአመክንዮም (Reason) አንጻር አሳማኝ ነው።የሚለው ከሥነ አፈታትም ይሁን ከአመክንዮ አንጻር ሚዛን የማያነሣ፤ ትክክለኛ ያልሆነ ድምዳሜ ነው።

የአንድ ነገር ትክክለኛ መሆን ወይም አለመሆን የሚለካው ከሆነ ነገር ጋር ተነጻጽሮ እንደሆነ አምናለሁ። እኛም የምናምነው ነገር ትክክል መሆኑን የምናውቀው በመጽሐፍ ቅዱስ ገምግመን አመለካከታችን ውሃ አንሥቶ፣ ሚዛን ደፍቶ ሲገኝ ብቻ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያቱን ለምን እንደጠራቸው በማር 3÷13-14 ላይ እንመለከታለንኢየሱስ ወደ ተራራ በወጣ ጊዜ እነዚያን የፈለጋቸውን ወደ እርሱ ጠራ፤ እነርሱም ወደ እርሱ ቀረቡ። ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ፥ ለማስተማርም እንዲልካቸው ዐሥራ ሁለቱን መርጦ «ሐዋርያት» ብሎ ሰየማቸው።ከዚህ ክፍል እንደምንረዳው የዐሥራ ሁለቱ ተልእዕኮ እና ሐዋርያነት ምንጩ የኢየሱስ ክርስቶስ ጥሪ ነው። የተጠሩበትም ዐላማ ግልጽ ሆኖ ተቀምጧል። የተጠሩለት ዐላማ ሁለት ነውከእርሱ ጋር እንዲሆኑእናለማስተማርም እንዲልካቸውነው። ታዲያ ሌሎቹ በአዲስ ኪዳን ውስጥምንመለከታቸው ሐዋርያት ተብለው የተጠሩ ነገር ግን ከዐሥራ ሁለቱ ወገን ያልሆኑ ሐዋርያት ይህንን ዕድል ስላላገኙ እንዴት ሐዋርያ ሆኑ? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሮአችሁ ሊመጣ ይችላል። ለዚህም ጥያቄሌሎቹን ሐዋርያት ተብለው የተጠሩትን ሰዎች ምላሽ ባላውቅም ጳውሎስ ምላሽ ሲሰጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመመልከት ችያለሁለአሕዛብ ስለ ልጁ የምሥራቹን ቃል እንዳበሥር እግዚአብሔር ልጁን ሊገልጥልኝ በወደደ ጊዜ እኔ ከማንም ጋር አልተማከርኩም”(ገላ 1÷16) ጳውሎስ ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱ እንዲያስተምሩ አንደላካቸው ሁሉ እኔንምየምሥራቹን ቃል እንዳበሥርልኮኛል ብሏል።

ይህ እንግዲህ በኢየሱስ የምሥራቹን ወንጌል ያበሥሩና ያስተምሩ ዘንድእርሱ በቀጥታ የተላኩ ሰዎችን ቁጥር ከ12 በላይ ያደርገዋል። ምክንያቱም ጳውሎስ፣ ባርናባስ ለአንዲራኒቆንና ለዩልያን[8]፣ የጌታ ወንድም ያዕቆብ[9]፣ ጢሞቴዎስ[10] ((ሐዋ14÷4፤ 1ቆሮ 9÷6፤ ሮሜ 16÷7፤ ገላ 1÷19፣ 1ተሰ 2÷6) እና ሌሎችም ከዐሥራ ሁለቱ እኩል የክርስቶስ ሐዋርያት ተብለው መጠራታቸውን ከመጽሐፍ ቅዱሳችን እንረዳለን። ነገር ግን ይህ የሐዋርያትን ቁጥር ገደብ የለሽ ያደርገዋል (እንደ አፈወርቅ ሀይሉ በየዘመናቱ ሐዋርያት ይነሣሉ) ወደሚል መደምደሚያ ግን አያደርስም። ወንድማችን አፈወርቅ ሀይሉ ከማቴቴስ መጽሔት ጋር በመጋቢ ዳንኤል “ሐዋርያዊ በዓለ ሥመት” ላይ በሰጡት የግል አስተየት ጰውሎስ “የግንባር ላይ ሥጋ ነው” ነው፤ እርሱ ሐዋርያ መሆኑን ከተቀበለን በዘመናችን ሐዋርያት መኖራቸውን መካድ አንችልም ብለውናል። እኔ ግን ይህ የተሣሣተ ድምዳሜ ነው እላለሁ። ምክንያቱም ጳውሎስ 1ቆሮ 15÷5-9 ላይ እርሱ ሐዋርያት ለመሆን ከተጠሩት እና ከተላኩት፤ የኢየሱስን የትንሣኤ አካል በዐይነ ሥጋ ከተመለከቱት ሰዎች መካከል የመጨረሻው እንደ ሆነ ገልጿል። ይህ ክፍል የሚያስረግጥልን በዐይነ ሥጋ የተመለከቱት ሁሉ ሐዋርያ ናቸው የሚለውን ሳይሆን የክርስቶስን ትንሣኤ አካል ለመመልከት ከታደሉት ሰዎች መካካል ጳውሎስ የመጨረሻ መሆኑን ነው። “እርሱ ለጴጥሮስ ታየ፤ ኋላም ለዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ታየ፤ ከአምስት መቶ ለሚበልጡ ተከታዮቹም በአንድ ጊዜ ታያቸው፤ ከእነርሱ አብዛኞቹ እስከ አሁን በሕይወት አሉ፤ አንዳንዶቹ ግን ሞተዋል። ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ታየ፤ ለሐዋርያትም ሁሉ ታያቸው:: በመጨረሻም እንደ ጭንጋፍ ለሆንኩት ለእኔ ደግሞ ታየኝ። እኔ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ያሳደድኩ ስለ ሆነ ከሐዋርያት ሁሉ ያነስኩና ሐዋርያም ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ ነኝ” (የ1980 ትርጉም)። “በመጨረሻም[11] የሚለው ቃል ትኩረት የሚያሻው ቃል ነው። ምንም እንኳ መጨረሻ የሚለው ቃል ከዚያ ለሌሎች ሰዎች አልታየም ወደሚል መደምደምያ የማያመራን ቢሆንም የጳውሎስ አጠቃቀም ግን ወደዚያ ያመራናል። ጳውሎስ ከተዘረዘሩት ሐዋርያት በኋላ ለእኔ ታየ ማለት ቢፈልግ ኖሮ “ከዚያም” የሚል ትርጓሜ ያለውን ቃል ይጠቀም ነበር። ነገር ግን ከዚያም (ἔπειτα) ከሚለው ቃል ይልቅ በመጨረሻም (e&sxaton) የሚለውን ቃል ተጠቅሟል። ጳውሎስ ይህንን ቃል የተጠቀመው ከእርሱ በፊት የነበሩት ክርስቲያኖች ይጠቀሙበትነበረውን የክርስቶስን ሞት እና ትንሳዔ ለማመልከት ይጠቀሙበት የነበረውን የእምነት መግለጫ በመጠቀም ነበር። ጳውሎስ ክርስቲያን ከመሆኑ በፊት የነበሩ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ከሞት መነሣት እና ለሐዋርያት መታየቱን የሚያመለክቱበት የእምነት መግለጫ ነበራቸው። ይህ የእምነት መግለጫ ከጳውሎስ ስም ውጭ 1ቆሮ 15÷5-9 ያለውን ይመስላል።[12] ጳውሎስ ይህንን የክርስቶስን ትንሣኤ እና ለሐዋርያት መታየቱን የሚያመለክት የእምነት መግለጫ እንዳለ በመውሰድ ራሱን ከሐዋርያት ጋር በማስተካከል 1ቆሮ 15÷5-9ን ጽፏል።[13] ይህ ታዲያ እንዴት ከጳውሎስ አልተገለጠም ወደሚል መደምደምያ ያመራናል? የሚል ጥያቄ ያስነሣል። ለዚህ ጥያቄ የእኔ ምላሽ የሚሆነው፣ በዚህ ክፍል ውስጥ የተጠቀሱት ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበትን የሐዋርያትን አስተምህሮ ያስተማሩ ሰዎች በመሆናቸው፤ ጳውሎስም ከእነዚህ የክርስቶስ ሐዋርያት በጊዜ ቅደም ተከተል የመጨረሻ በመሆኑ፤ እንዲሁም እንደ እነርሱ ቤተክርስቲያን የተመሠረተችበትን አስተምህሮ እርሱም በማስተማሩ ነው። ይህንን ሀሳብ ጳውሎስ እንዲህ ይገልጸዋል “እንግዲ እኔም ሆንሁ እነርሱ የምናስተምረው ይህንኑ ነው፤ እናንተም ያመናችሁት ይህንኑ ነው።” (1ቆሮ 17፡7) በማለት ኢየሱስ ለሐዋርያት የመገለጡ ምክንያት የተልእኮአቸው እና የአስተምህሮአቸው ምንጭ በመሆን ቤተ ክርስቲያንን እርሱ በአስተማራቸው አስተምህሮ መሠረት ይመሠርቱ ዘንድ ነው በማለት ገልጿል። ለዚህም ነው ጳውሎስእግዚአብሔር በሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልኅ ግንበኛ መሠረትን ጣልኩ፤ አንድ ጊዜተመሠረተው መሠረት በቀር ማንም ሌላ መሠረት መጣል አይችልም፤ ይህም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነውያለው። ስለዚህም ቤተክርስቲያን የተመሠረተችው በሐዋርያት አስተምህሮ መሠረት ላይ ከሆነ፤ ጳውሎስ ደግሞ የቤተክርስቲያን መሠረት የሆነውን አስተምህሮ ካስተማሩ ሐዋርያት በጊዜ ቅደም ተከተል የመጨረሻው ከሆነ፤ በዘመናችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ልኖሩ አይችሉም።

በተጨማሪም በዚህ ዘመን ሐዋርያት አሉ ወደሚል ድምዳሜ ላይ መድረስየዘመናችንን ሐዋርያት ነን ባዮችንአስተምህሮ ከተገለጠልን መጽሐፍ ቅዱስ ጋር ስለሚያስተካክለው ትክክል አይደለም። ምንም እንኳ ሁሉም ሐዋርያት መጽሐፍትን ባይጽፉም የእምነታችን ምንጭ ግን ከሞት ከተነሣው ክርስቶስ ባገኙት ሹመት ለእኛ ያስተላለፉልን አስተምህሮ ነው። የሐዋርያት የእምነት መግለጫን ሐዋርያው ጳውሎስ 1ቆሮ 15፡ 3-8 እንዲህ ይገልጸዋል እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ ለኬፋም ታየ በኋላም ለ[ዐ]ሥራ ሁለቱ፤ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፤ ከእነርሱም የሚበዙቱ እስከ አሁን አሉ አንዳንዶች ግን አንቀላፍተዋል፤ ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ፤ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ” (1962 ትርጉም)። እነርሱ ያስቀመጡልን እስተምህሮ ደግሞ ለደህነታችን በቂ ሆኖ ይገኛል። በመሆኑም በዚህ ዐይነት መልኩ “ሐዋርያት በዘመናችን አሉ” የሚለው አስተምሕሮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም። የኢየሱስን ትንሣኤ አካል በዐይነ ሥጋ ሳይመለከቱ ሐዋርያነት የለም።

እርግጥ ነውየዘመናችን ሐዋርያት ነን ባዮች” “አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናችን የተወሰነ ተግባር እንድንፈጽምላት በውክልና ልካን ነው” ካሉ፤ በአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ውስጥ የተጠቀሱትም ቤተ ክርስቲያናት ሰዎችን በእንደዚህ መልኩ ሲልኩ ስለምንመለከት ችግር የለውም ባይ ነኝ። (ይህንን ከላይ ከጠቀስኩት ቁ.3 ያለው ሀሳብ ልብ ይሏል) ቄስ ቶሎሳ ጉዲና እንዳሉትየዘመኑ ሐዋርያ ቤተ ክርስቲያን ወዳልተመሠረተችበት በመሄድ፣ ወንጌል ወዳልደረሰበት ሄዶ ቤተ ክርስቲያን ማቋቋም ነው።[14] እነዚህ ሰዎች “ሐዋርያነታቸውን” ሲገልጹ እርሳቸው እንዳሉት ወንጌል ወዳልደረሰበት ቦታ ወንጌልን ለመስበክ ተልከናል ከሆነ ሐዋርያ እና ሚስዮናዊነት እኩል ናቸውና እንግዲህ ወንጌል ወዳልደረሰበት ቦታ ሲሄዱ እንመልከት። እንዲሁ ከተማ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን እንደአሸን በፈላበት ቦታ ሆኖሚስዮናዊ ወይም ሐዋርያነኝ ማለት ግን አይቻልም፤ሐዋርያለመባል የመፈለጋቸው ምክንያት ሌላ ካልሆነ በስተቀር። ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን ከካቦድ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ፣ሐዋርያት ለቤተ ክርስቲያን የተሰጡ ናቸው ካልን ቤተ ክርስቲያን እስካለች ድረስ ሐዋርያትም ሊኖሩ እንደሚችሉ እየመሰከርን ነውብለዋል[15]:: ይህ አባባላቸው ልክ እንዳልሆነ ከዚህ በላይ ለማሳየት ሞክሪያለሁ። በመቀጠልም ምንም እንኳ በዘመናችን ያሉሐዋርያት" በመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ትምህርት ላይ በመደገፍበመስበክ እና በማስተማር መሠረት የሚጥሉ ናቸውብለዋል። እኝሁ ሰው የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ በማሳየት ወንጌል ወዳልደረሳቸው ቦታዎች በመሄድ ቤተ ክርስቲያንን የሚመሠርቱ ናቸው ብለዋል። “መሠረት የሚጥሉ ማለት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን የሚመሠርቱ” ከሆኑ እነዚህ ሚስዮናውያን ናቸው። “ሚስዮ” የሚለው ቃል የላቲን ቃል ሲሆን የሚያመለክተው መላክን ነው። ሚስዮናዊያን ወንጌል ወደልደረሳቸው ቦታዎች በመሄድ ወንጌልን እንዲሰብኩ በቤተ ክርስቲያን የሚላኩ ሰዎች ናቸው። ስለዚህ በዘመናችን የምንመለከታቸውሐዋርያነን የሚሉ ሰዎች ወንጌል ወዳልደረሰበት ቦታ በመሄድ ያሳዩን እላለሁ። ካልሆነ ግን እነዚህ ሰዎች ሐዋርያነታቸውን እንድንቀበል ሲጠይቁን ወንጌልን ወዳልደረሰበት ቦታ በመሄድ እንዲሰብኩ በቤተ ክርስቲያን መላካቸውን ሳይሆንየሐዋርያነት ሥልጣናቸውንእንድንቀበል እየጠየቁን ስለሆነ ጥያቄአቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ስለሌለው ተቀባይነት አይኖረውም።

ታዲያ የዘመናችን የሐዋርያነት ሹመት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቱ ምን ይሆን? ወንድማችን እስክንድር ታደሰ እንደሚለው እነ እከሌ ስላደረጉት እኛም እናድርገው ነው? “የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ አንግልካንስን ጨምሮ ሐዋርያነት በቅባትነት ወደ ሊቀ ጳጳስነት ተሸጋግሯል[16] ብለዋል። ራሳችንን ልንጠይቀው የሚገባን ነገር እነርሱ ይህንን ያደረጉት ወንጌልን ለመስበክ የተላኩ ሰዎች ናቸው በማለት ነው ወይስ የእነዚህን ሰዎች ሥልጣናቸውን ለማሳየት ነው? እኔ እስከማውቀው ድረስ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ እኩል ሥልጣን አለው የሚል አስተምህሮ ስላላት ነው።

እንዲሁም በቄስ ቶሎሳ ጉዲና ስም በካቦድ መጽሔት ላይ በወጣ ጽሑፍ ላይ “በታንዛኒያ ሉትራን ቤተ ክርስቲያን ሃያ አንድ ቢሾፖች አሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ቢሾፕ የለንም”[17] ብለዋል። “ቢሾፕ” ማለት ግን ምን ማለት ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሽማግሌ፣ መጋቢ እና ጳጳስ (ቢሾፕ) የሚሉ ቃላት የሚያመለክቱት አንድን ተግባር ነው። ይህውም መጋቢነትን ነው። (ቲቶ 1÷5-7፣ የሐዋ 20÷17፡ 28) “ሽማግሌ የሚለው ቃል የብሉይ ኪዳንን ታርካዊ ዳራ ሲኖረው ጳጳስ የሚለው ቃል ደግሞ የግሪክ ከተማዎች ጠባቂ (የከተማ አስተዳዳር) የሚል ታርካዊ ዳራ አለው።”[18] ነገር ግን እነዚህ ሥስት ቃላት የሚያመለክቱት አንድን ነገር ብቻ ነው። ይህውም መጋቢነትን ነው። ታዲያ መጋቢያን በሃገራችን የሉምን? ቄስ ቶሎሳ ጉዲና የተሾመ “ሐዋርያ” አንድም የለንም ለማለት ካልፈለጉ በቀር። ስለዚህ እኛም እንደነሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እኩል ሥልጣን ያለው “ሐዋርያን” እንሹም? በጭራሽየቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለችእንዳይሆንብን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል። ሐዋርያት እንዲኖሩን ብለን የድነታችን መሠረት የሆነውን የሐዋርያትን አስተምህሮ ሥልጣንን እና መሠረትን እንዳንሸረሽር ልንጠነቀቅ ይገባል። የሌለንን እንጨምር ብለን መጽሐፍ ቅዱስ ካስቀመጠልን ገደብ ማለፍ ፈጽሞ አይገባንም። ነገር ግን ወንጌል ወደልደረሰበት ቦታ ሄደው የምሥራቹን ወንጌል ለመናገር እግዚአብሔር ጸጋውን የሰጣቸው ሰዎች ይኖራሉና ቤተ ክርስቲያን እጆቿን ዘርግታ በደስታ ልትልካቸው ይገባል እላለሁ።

ይህን ሁሉ እንዲል ያደረገኝ በወንጌል ብርሃን ቤተክርስቲያን የመጋቢያቸውን “የሐዋርያዊ አገልግሎት” እውቅና ለመስጠት ሽር ጉድ በሚሉበት ሰዓት በቤተክርስቲያኗ ሥነ-ጽሑፍ ክፍል ይዘጋጁ የነበሩ ጽሑፎች የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ከማንጸባረቅ ይልቅ ሀሳባቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ በማስመሰል፤ በሰው ልብ ውስጥ ለማስረጽ የሚደረጉ ሙከራዎች በመሆናቸው ነበር። ለምሳሌ ያክል በወንጌል ብርሃን ቤተ ክርስቲያን “የሐዋርያነት ጸጋ ምንድን ነው? ለምን አስፈለገ? እንዴት እንጠቀምበት?” በሚል ርእስ በተዘጋጀ ብሮሸር ላይ የተገለጸው የሐዋርያነት ትንታኔ በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ሲታይ እውነታነት ይጐድለዋል። አደጋውም የሰፋ ነው። ጽሑፉም ስለ ሐዋርያነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮን ከማስተላለፍ ይልቅ ቤተ ክርስቲያኗ መጋቢዋን የ“ሐዋርያነት አገልግሎት” ዕውቅና ለመስጠት ማቀዷን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል የታለመ ነው። ይህን በድፍረት እንድል ካነሣሡኝ በጽሑፍ ውስጥ ካገኘሁት አንድ ምሳሌ ለእማኝነት ልጥቀስ “. . . ሐዋርያት ከጳውሎስ ጀምሮ እስከዚህ ዘመን በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉትን ይመለከታል። [ዐ]ሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ከበዓለ ኀምሳ በፊት በነበረው የጌታ አገልግሎት የተሳተፉ የትንሣኤው ምስክሮች ሲሆኑ፣ ጳውሎስና ሌሎች ሐዋርያት ከበዓለ ኀምሳው በኋላ የመጡ ናቸው። ሆኖም በ2ኛ ቆሮ 12÷12 መሠረት ቀጣዮቹ ሐዋርያት በድንቅና በተአምራት፣ ወንጌልን ማስተማራቸውና [ቤተ ክርስቲያንን] መትከላቸው የሐዋርያቱ አገልግሎት መገለጫ ሆኗል፣ ዛሬም ይቀጥላል።” ብሏል። ሐሳባቸውን ያጠናክርላቸውም ዘንድ ከበዓለ ኀምሳ በኋላ ሐዋርያ የሆኑትን የጳውሎስን፣ ባርናባስን እና የጌታ ወንድም የሆነውን የያዕቆብን ስም ለዋቢነት አቅርበዋል። የቤተ ክርስቲያኗ የሐዋርያነት ትንታኔ መንፈስ ቅዱስ የወረደበትን የበዓለ ኀምሳ ቀንን መሠረት በማድረግ ሐዋርያቱን በሁለት ጎራ ከፍላ ትመለከታለች። ቅድመ እና ድህረ በዓለ ኀምሳ ሐዋርያት። ቅድመ በዓለ ኀምሳ ሐዋርያት ዐሥራ ሁለቱ ሲሆኑ፤ ድህረ በዓለ ኀምሳ ሐዋርያት ከነ ጳውሎስ፣ ያዕቆብ እና ባርናባስ ጀምሮ በእኛ ዘመን እስካሉት “ሐዋርያት” እንዲሁም በመጭውም ዘመን የሚመጡትን ያጠቃልላል። ይህ ከሆነ ቤተ ክርስቲያኒቷ ግርድፍ በሆነ፣ ድህረ በዓለ ኀምሳ ሐዋርያት በሚል ትርጓሜ መጋቢያቸውን እና ጳውሎስን በሐዋርያነተታቸው እኩል እያደረጉ ነውና፤ ሐሳባቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እጅግ የራቀ እና ስህተት ነው። ከኑፋቄነት ተርታ የሚመድብም ነው።

ከዚህ በተጨማሪ የወንጌል ብርሃን መጋቢ ጸጋቸው እና አገልግሎታቸው “ሐዋርያዊ” ስለነበር እውቅና ለመስጠት ነው በሚል በቤተክርስቲያኗ እየተሰራጨ የነበረው ሀሳብ እውነታነት ይጎለዋል። ምክንያቱም ጸጋዎች ሁሉ ለቤተክርስቲያን መታነጽ የሚሰጡ መሆኑን፤ እንዲሁም እኩል መሆናቸውን ካመንን እስከ ዛሬ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የተለያዩ አገልጋዬች በልዩ ልዩ ጸጋ ስያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፤ ነገር ግን የአንዳቸው የአገልግሎት ጸጋ እንዲህ ድል ባለ ድግስ እና ፕሮፖጋንዳ እውቅና ስሰጠው አልተመለከትንም። ስለዚህ መጋቢያቸውን “የሐዋርያነት አገልግሎት እውቅና” አላማ በእርግጠኝነት ከጸጋ እና አገልግሎት ጋር ተያያዥነት የለውም፤ በውስጡም “የሐዋርያነትን”ሥልጣን መሻትን ያዘለ ነው።

ለማጠቃለል ያህል በአዲስ ኪዳን ውስጥ ሐዋርያ የሚለው ቃል ሁለት ዐይነት ትርጓሜ ይዞ ይገኛል። የመጀመሪያው “የተላከ” የሚል ትርጓሜ ሲኖረው ሁለተኛው እና በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተለመደው የቃሉ ትርጓሜ ግን የሚያመለክተው የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት (avpo,stoloj Cristou/ VIhsou/) በመባል የሚታወቁትን የአገልግሎት ቢሮን ነው። በሁለተኛው መልክ የተገለጸው የቃሉ አጠቃቀም ሐዋርያቱ ልዩ ሥልጣን እና ተልእኮ እንዳላቸው ልብ ይሏል። በዚህ መልኩ ሐዋርያ ለመባል ሁለት መስፈርቶችን ማሟላት አስፈላጊ ይሆናል። እነርሱም (1) ኢየሱስ ክርስቶስን በትንሣኤ ሥጋ መመልከት፣ (2) ሐዋርያ ሆኖ በኢየሱስ መሾም እና መላክ ናቸው። ምንም እንኳ አዲስ ኪዳን የእነዚህን ሐዋርያት ብዛት ይህን ያህል ነው ብሎ ባይገልጽልንም ነገር ግን በቁጥር የተወሰኑ መሆናቸውን ግን በአዲስ ኪዳን ውስጥ በግልጽ መመልከት እንችላለን። ሐዋርያ ለመባል በአዲስ ኪዳን ከተጠቀሱ መስፈርቶች ማሟላት በዘመናችን አይቻልም። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ወንጌል ወዳልደረሰበት ሄደው ወንጌልን ለመስበክ ሸክሙ እና ጸጋው ያላቸው ሰዎችን በመለየት ልትልካቸው ይገባል። እነዚህ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ በቀጥታ የተላኩ ሳይሆኑ፤ በቤተ ክርስቲያን የተላኩ በመሆናቸው የቤተ ክርስቲያን “ሐዋርያት” ወይም “የቤተ ክርስቲያን መልእክተኞች” ወይም “ሚስዮናዊያን” (avpo,stoloi evkklhsiw/n) ብለን ብንጠራቸው የስያሜ ለውጥ እንጂ አገልግሎታቸው አንድ ነው። ይህውም ወንጌልን ወዳልደረሰበት ማድረስ ወይም ቤተክርስቲያን እንዲፈጽሙላት የላከቻቸውን ተልዕኮ መፈጸም ነው። ስለዚህ በዘመናችን “ሐዋርያ” ለመባል ወይም “የሐዋርያዊ አግልግሎታቸው” ዕውቅና “የተሰጣቸው” ሰዎች ወይም “ሐዋርያ ተብለው የተሰየሙ ሰዎች” ሹመታቸው ወንጌልን ወዳልደረሰበት ለማድረስ ከሆነ እሰየሁ እላለሁ። ነገር ግን ፍላጎታቸው የሐዋርያትን ቢሮ እና ስልጣንን ከሆነ ግን ቆም ብለው ድርጊታቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ይፈትሹ ዘንድ ወንድማዊ ምክሬን እለግሳለሁ። የጽሑፍ እና የደጋፊ ጋጋታ ትክክል ያልሆነን ነገር ትክክለኛ ኣያደርገውም፤ እንዲሁም ከተጠያቂነት ኣያስመልጥምና ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል። ለዛሬው በዚህ አበቃሁ።



[1] እስክንድር ታደሰ፣ “የሐዋርያነት ጸጋ የመሳትም ሆነ የማሳት []ቅም የለውም፣” ካቦድ፣ ነሐሴ 2001 ዓም ቁጥር 4

[2] ዝኒ ከማሁ

[3] Gerhard Kittle and Gerhard Friedrich, Theological Dictionary of the New Testament. Electronic ed. Pc studay Wm. B. Eerdmans, 1972-1989

[4] ዝኒ ከማሁ

[5] እስክንድር ታደሰ፣ “የሐዋርያነት ጸጋ የመሳትም ሆነ የማሳት []ቅም የለውም፣” ካቦድ፣ ነሐሴ 2001 ዓም ቁጥር 4

[6]me,cri katanth,swmen ይህንን ሀረግ በRobertson Nicoll የተጻፈው The Expository Greek Testament መጽሐፍ እንዲህ ይፈታዋል ይህ “ፍጻሜን ያገኝ ዘንድ የክርስቶስ ስጦታ እና አቅራቦት መሰጠቱን የሚያመለክተው ዓረፍተ ነገር ተከትሎ የመጣው ጊዜ አመልካች ዓረፍተ ነገር በመሆኑ፤ ይህ አቅራቦት እና የሚያስከትለው አገልግሎት እስከመጨረሻው ይቆያል ወይስ የመጨረሻውን ውጤት ያመለክታል የሚለውን መለየት አለብን። . . . (በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የግሪኩን ዓረፍተ ነገር አወቃቀር መተንተን ለዚህ ጽሑፍ አስፈላጊ አይሆንም። ማመሳከር ለሚፈልግ ሰው ግን በዚህ ግርጌ ማስታወሻ ያሉትን መጽሐፍት መመልከት ይችላል።) እኚህ ሰው የግሪኩ የዓረፍተ ነገር አወቃቀርን ካስረዱ በኃላ ድምዳሜያቸውን katanth,swmen የሚለው ቃል የሚያስተላልፈው ከግብ መድረስ የሚለው ሀሳብ ነው።” በማለት የደረሱበትን ድምዳሜ አስቀምጠዋል። ይህንን ትርጓሜ የሚደግፉት የግሪክ ቋንቋ ምሁራን Daniel B. Wallace, Greek Grammar Beyond the Basics, An Exegetical Syntax of the New Testament (Zondervan: Grand Rapid Michigan) 2003 ገጽ 479-480፤ BDAG, Greek-English Lexicon of the New Testament and Other Early Christian Literature, (The University of Chicago: USA) 2000, ገጽ 517 እንዲሁም Bratcher R.G. and E.A. Nida, A Handbook on Paul's Letter to the Ephesians (United Bible Societies, New York) 1982.

ከዚህ በተጨማሪ me,cri የሚለው ቃል መስተዋድድ ቢሆንም ከእርሱ ቀጥሎ የመጣው katanth,swmen የሚለው ቃል subjunctive case ስለሆነ me,cri የሚለው ቃል የሚኖረው ትርጓሜ መስተዋደዳዊ (እስከ) ሳይሆን ንኡስ መስተፃምራዊ (እስከ) መሆን አለበት። “The prep. me/xri ‎occurs 17 times in the NT (the form ‎me/xri$ ‎appears only before vowels, in Mark 13:30; Gal 4:19; Heb 12:4). It functions 3 times as a conj. (twice in the combination ‎me/xri$ ou!‎, in Mark 13:30 and Gal 4:19; once alone, in Eph 4:13) and 14 times as a prep.: of space (Rom 15:19), of time (Matt 11:23; 28:15; Luke 16:16; Acts 10:30; 20:7; Rom 5:14; 1 Tim 6:14; Heb 3:14; 9:10), and expressing degree of suffering — unto death (‎me/xri qana/tou‎, Phil 2:8,30), bondage as a criminal (‎me/xri desmw=n‎, 2 Tim 2:9), or shedding blood (‎me/xri$ ai%mato$‎, Heb 12:4).” BAGD s.v.; BDF index s.v. I (Horst Balz and Gerhard Schneider, Exegetical Dictionary of the New Testament, escatoj electronic ed. Pc Study Bible 5. Grand Rapid, Michigan: William B. Eerdmans, 1990) የዚህን ስዋሰዋዊ መርህ ትክክለኛነት ለማመሳከር ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መጽሐፍት ይመልከቱ። በመሆኑም የ1980 ዓም የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ኤፌ 4፡13 ላይ የመጀመሪያው ቃል “እንዲሁም” መሆኑ ይህ ቃል ቀጠሎ ያለውን ዓረፍተ ነገር ከእርሱ በፊት ካለው ዓረፍተ ነገር ጋር የማጣመር አገልግሎትን ይሰጣል። “katanth,swmen” የሚለው ቃል ደግሞ “ደርሰን” በሚል ግብን በሚያመለክት ቃል ተተርጎሞአል። በመሆኑ እዚህ ከፍል ላይ የ1980 ዓም የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ትክክለኛውን የግሪኩን ስዋሰዋዊ የአተረጓጎም መርህን የተከተለ መሆኑን እንገነዘባለን።

[7] በሐዋርያት እና በነብያት መሠረት ላይ መገንባት የሚለውን ሀሳብ የሚገልጸው ዓረፍተ ነገር የስዋሰው ቀመሩ በgenetive case ስለሆነ በጥንቃቄ መመልከት የሚጠይቅ ነው። tw/n avposto,lwn kai. profhtw/n( የሚለው ሀረግ የግሪክ ስዋሰዋዊ አወቃቀር በሶስት ዓይነት መንገድ መረዳት እንደምቻል የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ይናገራሉ። እነርሱም፦ (1) genitive of appostion= the foundation which is or conists in the Apostle; (2) the gen. of origination cause= the foundation laid by them; (3) the possess gen.= ‘the Apostle’ foundation”- in the sense of that on which they built 0r as = that on which they also were built. The chose seems to be between (1) and (2). ከእነዚህ አማራጭ ትርጓሜዎች ውስጥ ከክፍሉ እና ከአጠቃላዩ የመጸሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ጋር ተቀራራብ የሆነው በቁ. 1 ላይ የተገለጸው እንደሆነ ኣስባለሁ። በዚህም መሠረት ሐዋርያት እና ነብያት የቤተ ክርስቲያን መሠረት ሆነው እንዳገለገሉ ጸሐፍው በምሳሌዊ አነጋገር ገልጿል። የመጸሐፉ ጸሐፊ ቤትን እንደ ምሳሌ በመውሰድ ሐዋርያትን እና ነቢያትን የዚህ ቤት መሠረት እንደሆኑ፤ እንዲሁም አሕዛብ እና አይሁዳዊያን በዚህ መሠረት ላይ መገንባታቸው፤ ነገር ግን ሁሉንም አያያዥ ሆኖ የሚያገለግለው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ገልጸዋል። ከዚህ ክፍል በመቀጠል ሐዋርያት እና ነቢያት መሠረት ሆነው እንዴት እንዳገለገሉ አሳይቷል። ይኸውም እግዚአብሔር በእነርሱ አማካኝነት ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበትን ባለፉት ብሉይ ኪዳን ዘመናት ለማንም ያልተገለጠው ምስጥር እግዚአብሔር ለሐዋርያቱ እና ለነቢያቱ በዚህ ዘመን በመገለጡ ምክንያት ሐዋርያት እና ነቢያት በዚህ በተገለጠላቸው፤ በክርስቶስ ሞት እና ትንስኤ የሚገኘውን ድህነት፣ አሕዛቦችም ወራሾች እንደሆኑ ባስተማሩት አስተምህሮ፣ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እንደሆኑ በኤፌ 3፡5 ላይ እንመለከታለን።

[8] እነዚህ ሰዎች ሐዋርያት ሳይሆኑ በሐዋርያት መካከል የታወቁ ሰዎች እንደሆኑ የሚከራከሩ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ፤ ነገር ግን ይህ ክፍል ሃሳባቸው አይደግፍላቸውም ብዬ እሞግታለሁ። ይህን አመለካከት እኔ ብቻ ሳልሆን ሌሎች በጣም የታወቁ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ይጋሩታል “oi{tinev" eijsin ejpivshmoi ejn toi`" ajpostovloi", oi} kai; pro; ejmou` gevgonan ejn Cristw`/, “who are outstanding among the apostles, who also were in Christ before me.” ejpivshmo", “splendid, outstanding, prominent” (BGD). The full phrase almost certainly means “prominent among the apostles,” rather than “outstanding in the eyes of the apostles" (Dunn, James D.G., Word Biblical Commentary, Volume 38b: Romans 9-16, (Dallas, Texas: Word Books, Publisher) 1998.)

[9] በገላቲያ 1፡19 ላይ ያለውን e{teron de; tw`n ajpostovlwn oujk ei\don, eij mh; ÆIavkwbon to;n ajdelfo;n tou` kurivou, “I did not see any of the other apostles—only James, the Lord’s brother.” The major issue of v 19 is whether James is classed by Paul among the apostles (cf. v 17) or distinguished from them. The question has usually been discussed in terms of whether the idiomatic expression eij mhv (“except,” “only”) which has exceptive force, refers to the whole clause, “I did not see any of the other apostles,” or only to the verb, “I did not see.” The latter is possible (cf. 2:16; also Matt 12:4; Luke 4:26–27; Rev 21:27). Yet as Lightfoot pointed out, “the sense of e[teron naturally links it with eij mhv, from which it cannot be separated without harshness, and e{teron carries tw`n ajpostovlwn with it” (Galatians, 84–85). So with Light foot most have concluded: “It seems then that St James is here called an Apostle, though it does not therefore follow that he was one of the Twelve” (ibid., 85; cf. Acts 9:27). L. P. Trudinger has argued that e{teron, “other,” here has a comparative force that differentiates (“other than the apostles”) and so excludes James from the apostles (NovT 17 [1975] 200–202). George Howard, however, observes that while such a use of e{teron is possible, the examples cited by Trudinger from classical literature to support his thesis actually compare persons or things of the same class; and he further rightly argues that if Paul wanted to distinguish James from the apostles, he would have written e{teron de; h] tou;" ajpostovlou", “other than the apostles,” or used e{teron in combination with parav, “than,” or the dative case (NovT [1977] 63–64). Thus whatever ambiguity remains in this verse about James being classed among the apostles, it has to do with the referent of eij mhv and not with the use of e{tero". And this being so, e{teron here should probably be seen as enumerative and not differentiative, eij mhv as referring to the whole previous clause, and James as included among the apostles (also, then, among the tou;" pro; ejmou` ajpostovlou", “apostles before me,” of v 17).” (Longenecker, Richard N., Word Biblical Commentary, Volume 41: Galatians, (Dallas, Texas: Word Books, Publisher) 1998.)

[10] ምንም እንኳ አንዳንድ የመጽሐፍ ምሁራን ጢሞቴዎስ በዚህ ስፍራ ሐዋርያ ተብሎ አልተጠራም ብለው ቢሞግቲም በዚህ ክፍል ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ከእርሱ ጋር ሐዋርያ እንደሆነ የተጠቀመው የግሪክ ቋንቋ ስዋሰው ግልጽ እንደሚያደረደረጉ ምሁራን ይናገራሉ።wJ" Cristou` ajpovstoloi, “as Christ’s messengers.” Here ajpovstolo" is used in a rather general sense: Paul associates his companions with his own apostolic ministryin which indeed they shared. Paul normally gives ajpovstolo" a wider range of meaning than does Luke (who, apart from the reference to Paul and Barnabas in Acts 14:4, 14, restricts it to the twelve), but the special sense in which he uses the term—e.g. when he groups James the Lord’s brother with “all the apostles” in 1 Cor 15:7 (cf. Gal 1:19) or refers in Rom 16:7 to Andronicus and Junia(s), who were “in Christ” before himself, as “noteworthy among the apostles”—an scarcely be stretched to include Timothy, his own “son in the faith” (1 Tim 1:2), whatever may be said of Silvanus. If one may judge from Paul’s account of the origin of his own apostleship, he appears to use the term of one who had seen the risen Lord and had been commissioned by him (whether alone or in a company with others).” Bruce, F.F., Word Biblical Commentary, Volume 45: 1 & 2 Thessalonians, (Dallas, Texas: Word Books, Publisher) 1998.

[11] በ1980 ዓም ትርጉም “በመጨረሻም” ተብሎ የተተረጎመው “escaton pa,ntwn” የሚለው የግሪኩን ቃል በ1954 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም “ከሁሉ በኋላም” በሚል ተተርጉሟል። በሥነ-መለኮት ምሁራን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው BDAG የተባለው Greek-English Lexicon of the New Testament and Other Early Christian Literature, “escaton” electronic ed. Bibleworks 6 (The University of Chicago: USA) 2000, ገጽ 314 ላይ የቃሉን ፍች እንዲህ ያስቀምጠዋል “With reference to a situation in which there is nothing to follow”። እንዲሁም ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር እንዲህ ይላል Paul himself sought to establish the limited extent of the numbers of apostles. His careful words that Christ “appeared to me last of all” (1 Cor 15:8) serve to show that while there were apostles before him, there were no apostles after him. According to Paul he is both “the least” and “the last” of the apostles.” (Hawthorne, G. F., R. P. Martin, & D. G. Reid. Dictionary of Paul and His Letters. “Apostle” electronic ed. Logos Library Systems. Downers Grove: InterVarsity, 1997, c1993. P.50). በተጨማሪም escatoj የሚለው ቃል TDNT የተባለው የአዲስ ኪዳን የሥነ መለኮት መዝገበ ቃለት የዚህን ቃል ትርጓሜ ሲሰጥ እንዲህ ይላል “The general use of the term for something which is last either materially (Matt 5:26; Luke 12:59) or in space (Acts 1:8; 13:47: e%w$ e)sxa/tou th=$ gh=$) or time (Matt 12:45; 20:8ff.; 27:64; Mark 12:6,22; Luke 11:26; John 7:37; 2 Peter 2:20; Rev 2:19), becomes theologically significant, at least indirectly, in 1 Cor 15:8, in the e&sxaton of the final resurrection appearance to Paul. The association of littleness with the last, gives to this Pauline experience its character as e&ktrwma. At the same time, e&sxaton suggests the closing of a series, so that from the time of this e&sxaton there can be no similar or equivalent events.” (Gerhard Kittle and Gerhard Friedrich, Theological Dictionary of the New Testament. Electronic ed. Pc studay Wm. B. Eerdmans, 1972-1989 .) ስለዚህም የ1980 “በመጨረሻም” ይሁን የ1954 “ከሁሉ በኋላም” የሚያመለክተው ጳውሎስ ኢየሱስን ከትንሳዔ በኋላ ከተመለከቱት የመጨረሻው እንደሆነ፤ ከእርሱ በኋላም የኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሳዔ በኋላ የተመለከተ አለመኖሩን ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ (avpo,stoloj Cristou/ VIhsou/) ተብሎ ለመጠራት ኢየሱስ ክርስቶስን ከትንሳዔ በኋላ መመልከት አንዱ መስፈርት በመሆኑ፤ ከጳውሎስ በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስን የተመለከተ ሰው ባለመኖሩ ምክንያት ሐዋርያት ተብሎ የተጠራም ይሁን ልጠራ የሚገባው አለመኖሩን ይህ ክፍል ያረጋግጥልናል። ስለዚህም ከጳውሎስ በኋላ ሐዋርያ በለመኖሩ ምክንያት በዚህ ዘመን ሐዋርያት አሉ የሚለው አመለካከት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አይኖረውም።

[12] Hawthorne, G. F., R. P. Martin, & D. G. Reid. Dictionary of Paul and His Letters. “Apostle” electronic ed. Logos Library Systems. Downers Grove: InterVarsity, 1997, c1993. P 4

[13] Horst Balz and Gerhard Schneider, Exegetical Dictionary of the New Testament, escatoj electronic ed. Pc Study Bible 5. Grand Rapid, Michigan: William B. Eerdmans, 1990. Paul understands himself as standing in the succession of the apostles; at the same time the succession of witnesses to Easter is concluded with him (15:3-10). He takes up the pre-Pauline confessional statement (probably up to v. 5) and extends the line of Easter witnesses up to himself: "But last of all he appeared . . . also to me" (v. 8). Thus he designates himself as irrevocably the last in a series but at the same time disqualifies himself (cf. 4:13) as one who does not belong precisely in the series, but nevertheless stands at the end (15:8: "miscarriage"; v. 9: "the least of the apostles").”

[14] ካቦድ፣ ነሐሴ 2001 ዓም ቁጥር 4 ላይ ቄስ ቶሎሳ ጉዲና የሰጡት አስተያየት

[15] ካቦድ፣ ነሐሴ 2001 ዓም ቁጥር 4 ላይ ከወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

[16] እስክንድር ታደሰ፣ “የሐዋርያነት ጸጋ የመሳትም ሆነ የማሳት []ቅም የለውም፣” ካቦድ፣ ነሐሴ 2001 ዓም ቁጥር 4

[17] ካቦድ፣ ነሐሴ 2001 ዓም ቁጥር 4 ላይ ቄስ ቶሎሳ ጉዲና የሰጡት አስተያየት

[18]Bob Utley, Study Bible New Testament supplement, “Ephesians” (Bible Lessons International) 2005. the concept of the shepherd and tending the flock is often found in association with that of the bishop or overseer and overseeing (cf. Jer 23:2; Ezek 34:11; Zech 11:16; CD 13.7–11, where the meðbaqqeµr, “guardian, overseer,” in the Qumran community is likened to a shepherd with his flock; Acts 20:28, where those appointed bishops of the church at Ephesus are to shepherd the church of God; 1 Pet 2:25; 5:2; Ign. Rom. 9.1; Phil. 2.1, where the bishop is also called a pastor). It is probable, then, that the pastor of Eph 4:11 fulfills the functions denoted in Paul’s writings by such terms as proi>vsthmi, “to rule, manage” (1 Thess 5:12; Rom 12:8), kubevrnhsi", “administration” (1 Cor 12:28), and ejpivskopo", “bishop, overseer” (Phil 1:1). ejpivskopo" was a term taken from the Hellenistic world, but because the general notion of overseeing had close associations with the shepherd in Jewish thought, it is understandable that the term “pastor” could become interchangeable with “bishop” in the Christian movement. It is the equivalent to presbuvtero", “elder,” of Acts 14:23; 20:17; 1 Tim 4:14; 5:17, 19; Titus 1:5; 1 Pet 5:1, 5; Jas 5:14) (Lincoln, Andrew T., Word Biblical Commentary, Volume 42: Ephesians, (Dallas, TX: Word Books, Publisher) 1998.

Comments

  1. This comment has been removed by the author.

    ReplyDelete
  2. Good Job!!!!

    May God use us to His glory and the edification of His Church.

    Tesfaye Robele

    ReplyDelete

Post a Comment