“በዱሮ በሬ ማን አረሰ?”
“በዱሮ በሬ ማን አረሰ?”
በተካልኝ ዱጉማ
በማቴቴስ መጽሔት ቁጥር 9 እትም ላይ “የሚክያስን ወልድ ሥጋን ነሥቷል”ን እንቀበልን? በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ጽሑፍ ላይ በቁጥር 10 ላይ ሁለት ጠንካራ ሂሶች ተሰንዝረውበታል። ይህ በሀገራችን ሥነ-መለኮት እድገት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ስላለው እሰየው እደጉ ተመንደጉ እላለሁ። ከተሰጡት ሂሶች ውስጥ በወንድም ሚክያስ የቀረበው ትክክለኛ ሂስ ሆኖ ስላገኘሁት ከተወሰነ ማስተካከያ ጋር ተቀብዬዋለሁ። ይኸውም ሚኪያስ በማቴቴስ መጽሔት ቁጥር 8 ላይ “ወልድ ሥጋን ነሥቷል” በሚል ርዕስ ያቀረበው ጽሑፍ አለማ ላይ ያስቀመጠው ሂስ ነው። እንዲህ ይላል “የእኔ መልዕክት የሚያበቃው ክርስቶስ ኢየሱስ በእኛ ላይ ያለውን የኋጢአት ዕዳ፤ ዕዳው ያስከተለውን ሞት እና የዳቢሎስን እስራት ለመፍታት ሥጋን ተካፍሏል የሚለው ላይ ብቻ ነው፤ ነበር።” ይህ እውነት ነው የጽሑፋቸው ግብ ይህ ብቻ ነበረ። ነገር ግን “. . . ዓይኖቻችን ከፍተን እዚያ ሠፈር ያለውን መልካሙን ዘር ለመቃረም እንሞክር” የሚለው ግብዣቸው ግን ከጽሑፋቸው አላማ በመውጣት “እዚያ” መንደር ለመሄድ ስለሚጋብዘን እዛኛው ሠፈር ምን አለ? የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አደረገኝ። ለእርሳቸውም ግብዣ ““የሚክያስን ወልድ ሥጋን ነሥቷል”ን እንቀበልን? በማለት ምላሽ አሰጥቶኛል። ከእርሳቸው ጽሑፍ ያልተቀበልኩት “መላምት” ያሏትን ሀሳብ ነው። እርግጥ ሀሳቧ ወንድማችን ሚከያስ እንዳላት “መላምት” ወይም ወንድማችን ሰለሞን እንዳለት “በስማ በለው” የተገኘች ሳትሆን በቤተክርሰቲያኗን የአሁን ዘመን የእምነት ግለጫ መሰረት ያደረገች ሀሳብ በመሆኗ ጽሑፌን እና ዋቢ ያደረግሁትን የዘመኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫ እንደገና ያነቡ ዘንድ እጋብዛለሁ።
በሌላ በኩል ደግሞ ከሃያስያኑ መካከል በወንድም ሰለሞን የተሰጠኝ ሂስ ትንሽ የኔን የመከራከርያ ነጥብ ብዥታ ውስጥ ይጨምረዋል ብዬ ስላሰብኩ የባለፈው የጽሔፌን ዋና ሀሳብ ታጠናክርልኝና ይበልጥ ትገልጥልኝ ዘንድ ይችህን ትንሽ ጽሑፍ ላቅርብ። በአለፈው ጽሑፌ የእኔ መከራከሪያ ነጥብ መሰረት የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአሁን ጊዜ የእምነት አቋም መግለጫ እንጂ በታርክ ውስጥ የነበራት አስተምህሮ አልነበረም። ይህንን ሀሳብ ባለፈው ጽሑፌ እንዲህ ገልጬው ነበር “የአምላክ ሰው የመሆን ምሥጢር በቤተክርስትያን ታሪክ ውስጥ ብዙ የቤተክርስትያን አባቶችን እንዲያስቡበት እናም ምን ማለት እንደሆነ ለማስረዳት እንዲሞክሩ አስገድዶአቸዋአል፡፡ ዛሬ የቤተክርስትያን አባቶች ስለ ክርስቶስ ሰውነት ምን አሉ የሚለውን ለመዳስስ ሳሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን ከማርያም ነሥቶአል ማለት ምን ማለት እንደሆነ አሳያለሁ፡፡” ይህንንም ሀሳብ ለማስደገፍ በማስረጃነት ያቀረብኩትን ሀሳብ በቀናነት ከተመለከቱት የዘመኗ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኦፍሴላዊ የእምነት መግለጫዬ ነው ብላ ካቀረበችው መጽሐፍ የተወሰደ ነው። ይህንን ግን በተለይ ወንድማችን ሰለሞን በደንብ አልተረዱልኝም። ለዚህም ነው “ወንድማችን እንደ ቀልድ በወረወሯት ሀሳብ ለዘመናት በጸና መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ እና ድልብ ትፍት ጋር ተፋጠዋል።” በማለት የጻፉት። ነገር ግን ይህ “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” ነው። እኔ የቤተክርስቲያኗ የሥነ-መለኮት ትውፊት ትክክል ነውም አይደለምም አላልኩም። በእኔ ጽሑፍ ውስጥ በዋናነት የተጠቀሰው ነገር እንድንቃርም የተጋበዝነው የዘመኗ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምስጥረ ሥጋዌ አስተምህሮ ነበርና ይህ የዘመኗ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ትምህርተ ሥጋዌ “መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና በትውፍት የዳበረ” ከሆነ (የቤተክርስቲያኗ የዘመኑ አስተምህሮ በትውፍት እና በመጽሐፍ ቅዱስ የዳበረ ነው ከተባለ) ለመላተምም ሆነ ለመፋጠጥ ዝግጁ ነኝ። እኔ እንደማምነው የአንድ ቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫ የሚለካው ምን ያስተምር ነበር በሚል መስፈርት ሳይሆን አሁን ምን ያስተምራል በሚል መለክያ ነው። ቤተ እምነቶች በዘመናት መካከል ሥነ-መለኮታቸውን እንደለዋወጡ ከካቶሊክም ይሁን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ እንዲሁም በፕሮቴስታን አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ መመልከት እንችላለን። ዛሬ እኔ ወደዚያ ገብቼ እንዲህ እና እንዲህ ለማለት የዚህ ጽሑፍ አላማ ባለመሆኑ ትቼዋለሁ።
ወደ ተነሳሁበት ነጥብ ልመለስና የአንድ ቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫ የሚለካው በግለሰቦች አስተምህሮ፣ አልያም ባላቸው ሥነ-መለኮታዊ ታርክ ላይ ሳይሆን ቤተክርስቲያኗ በግልጽ የእምነት መግለጫዬ ነው ብላ ባስቀመጠችው አሁን በሚትጠቀምበት አስተምህሮ መዝገብ ውስጥ በሚገኘው አስተምህሮ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በአንድ ወቅት ትክክለኛ አስተምህሮ ያስተምር የነበረ ሁሉ ሁል ጊዜ ትክክለኛ ትምህርት ያስተምራል ማለት ስላልሆነ የአብያተክርስቲያናት የእምነት አቋም የሚለካው አሁን ባላቸው የእምነት መግለጫ (አስተምህሮ) መሆን አለበት።
አንድ ሌላ መጨመር የምፈልገው ነገር ቢኖር የቃላትን ትርጓሜ በጽሑፎቻችን ውስጥ ማስቀመጥ አግባብነት እና ጠቀሜታ እንዳለው አምናለሁ። ምክንያቱም ሰዎች የጽሑፉን ሀሳብን በግልጽ መረዳት ስለሚችሉ ግራ ከመጋባት እንዲሁም ሀሳባችን በተሳሳተ መንገድ እንዳይረዱት ያደርጋቸዋልና። ነገር ግን እኔ ከዚህ ቀደም ባቀረብኩት ጽሑፌ “የኦርቶዶክስ ሥነ-መለኮታዊ አፈር” ስል ሥነ-መለኮታዊ ታርክ ማለቴ እንዳልነበር ግልጽ ነው። ምክንያቱም አንድም ታርካዊ ሥነ- መለኮትን የሚያመለክት ነገር በጽሑፌ ውስጥ አልተጠቀምኩምና። ዋናው ነገር በማንኛውም ጽሑፍ ውስጥ የሚገለጹ ሀሳቦችን፣ ቃላትን ወይም የሀረጎችን ትርጓሜ ከጽሑፉ ሥነ-ጽሑፋዊ ዳራ አንባቢው በመመልከት መረዳት ይጠበቅበታል እንጂ ያለተባለው ማለት ግን አግባብነት አለው ብዬ አላምንም። ይህ ካልሆነ ግን “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ” የሚለው ብህል እውነት ይሆንና ጸሐፍው በጽሑፉ ማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት እና አንባቢው ከጽሑፉ የሚያገኘው መልዕክ ተለያይቶ አንባቢው እና ጸሐፍው በሀሳብ ሳይገናኙ መንገዳቸው ለየቅል፤ ድካማቸውም ከንቱ ድካም ሆኖ ይቀራል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዘመናት መካከል ያለፈችበትን ሥነ መለኮታዊ የእድገት ደረጃ በዚህ ጽሑፍ መግለጽ በሁለት ምክንያት አልችልም። አንደኛ ስለ እነርሱ የሥነ መለኮት እድገት ያለኝ እውቀት በጣም ትንሽ በመሆኑ፤ ሁለተኛ የዚህ ጽሑፍ አላማ ባለመሆኑ ናቸው። ስለዚህም “ያለ አዋቅ ሳሚ . . . ” እንዳይሆንብኝ እራሴን በተቻለ መጠን ገድቤ በዚህ ጽሑፍ ከተነሳሁበት ዓላማ ጋር ተዛማጅነት አላቸውን ብዬ የማምንባቸውን ለማንሳት እሞክራለሁ። በመጀመሪያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ማሪያምን ከመቼ ጊዜ ጀምሮ ማስተማር እንደ ጀመረች አሳያለሁ። በመቀጠልም በጥንቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የማሪያም አስተምህሮ ላይ የተጨመረው የማሪያም ኋጢአት ዬሌሽነት ትምህርት ከመቼ ወዲህ መሆኑን በማሳየት ይህ አስተምህሮ በአሁኗ የቤተክርስቲያኗ ትምህርተ ሥጋዌ ላይ ያለውን ተጽእኖ በማቅረብ በሁለቱ አስተምህሮዎች መካከል ያለው ግንኙነት አሳያለሁ።
የማርያም ከጥንተ አብሶ የሌሽነት አስተምህሮ እንዴት እና መቼ ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ገባ? ለሚየለው ጥያቄ ምላሽ የሚሆነው የተለያዩ የታርክ ማስረጃዎችን እንደሚያረጋግጡት ቤተክርስቲያኗ ስለ ማሪያም ከምስረታዋ 4ኛው ምዕተ ዓመት ጀምሮ እስከ 14 እና 15 ምዕተ ዓመት ድርስ ቤተክርስቲያኗ የኃይማኖት አባቶች ትምህርት የሆነውን ለእርሷ አክብሮትን እና ምስጋናን መስጠት፤ እንዲሁም ማሪያም እንደምትማልድ እና እርሷን ለሚፈልጉት እንደምትገለጥ በቋሚነት ታስተምር እንደ ነበር እንመለከታለን። ነገር ግን ከ14 ምዕተ ዓመት ጀምሮ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያለው የማሪያም ትምህርት በንጉሥ ዘርያዕቆብ ምክንያት ወደ ቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ በመጨመር የቤተክርስቲያኗን አስተምህሮ መለወጥ ጀመረ። “በዘርያዕቆብ ምሪት ማሪያም ኃጢአት አለባት ወይስ የለባትም የሚለውም ጥያቄ ልዩ ቦታ (በቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ ውስጥ) አገኘ። (በንጉሥ ዘረያዕቆብ ዘመን የተጻፈው) ታምረ ማሪያም ማሪያም በውሰት በአፍዎም ምንም ኋጢአት እንደ ሌለባት ይናገራል . . .” ። ይህን ያህል መቼ የማርያም ጥንተ አብሶ የሌሽነት ትምህርት ወደ ቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሰርጎ እንደገባ ካልኩ ይህ ትምህርት ደግም እንዴት ሌሎች የቤተክርስቲያኗ አስተምህሮዎች ላይ ትጽዕኖ ማምጣት እንደሚችል እናንተው ተመልከቱ።
በዘመኗ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ሥጋዌ አስተምህሮ መሠረት ወልድ “ሥጋ ነሣ” የተባለው ከቅድስት ድንግል ማሪያም ነው። “ወልድ ከሰማያት ወርዶ ከቅድስት ማሪያም ከሥጋዋ ሥጋን፣ ከነፍስ ነፍስ ነሥቶ በሥጋ የመገለጹ፣ አምለክ ሰው፣ የመሆኑ ምሥጢር ነው፡፡” ወልድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን መንሣቱን እኔም እስማማለሁ። ነገር ግን የቤተክርስቲያኗ የአሁን ግዜ ኦፌሳላዊ የእምነት መግለጫ መሠረት ያደረገው የማርያም ኋጢአት የለሽነት ነው ክርስቶስን ኋጢአት ዬለሽ ያደረገው በሚለው አስተምህሮ ግን በፍጹም አልስማማም። ምክንያቱም የቤተክርስቲያንቷ ኦፌሳላዊ መግለጫ እንዲህ ይላል “እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኀጢአት (ጥንተ አብሶ) ያላገኛት መርገመ ሥጋ ለፍስ የሌለባት ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ኀሊና ታስባ ትኖር ነበረች በሰው ልማድና ጠባይ ከሚደርሰው ሥጋዊ አሳብና ፍቃድ ሁሉ የተጠበቀች ከተለዩ የተለየች ንጽሕት ቅድስት ቅዱሳን ናት፡፡” ይህ አሁን ያለው የቤተከክርስቲያኗ የማሪያም አስተምህሮ ከዘርያዕቆብ ዘመን ጀምሮ የነበረ ነው:: ምንም እንኳ በዚህ ሀሳብ የማይስማሙ የቤተክርስቲያኗ የኃይማኖት ምሁራን ቢኖሩም። ሁለቱ (ትምህርተ ሥጋዌ እና ትምህርተ ማሪያም) የቤተክርስቲያኗ የአሁን ግዜ አስተምህሮዎች አንዱ በአንዱ ላይ ለመደገፉ በትምህርተ ሥጋዌ ውስጥ የጠቀሰው “ከቅድስት ማሪያም ከሥጋዋ ሥጋን፣ ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ” የሚለው ቃል እማኝ ነው። ለዚህ ሀሳብ አንዳንድ ሰዎች የቤተክርስቲያኗ ትምህርተ ሥጋዌ የተዘጋኘው ከተምህርተ ማሪያም በፊት ስለሆነ ምንም ግንኑኝነት የላቸው የሚል ታርካዊ ሥነ መለኮትን መሰረት ያደረገ ምላሽ ይሰጡ ይሆናል። ምንም እንኳ የቤተክርስቲያኗ ትምህርተ ሥጋዌ ከዚህ ጋር ተያያዥነት ካለው የማሪያም አስተምህሮ በጊዜ ቀደም ተከተል ቢቀድምም አሁን በቤተክርስቲያኗ የእምንት መግለጫ ውስጥ ያለው ትምህርተ ማሪያም በትምህርተ ሥጋዌ ላይ ተጽዕኖ ማምጣቱ ግን የማይቀር ነው። ምክንያቱም ሰዎች አንብበው የሚረዱት አሁን ያለው የቤተክርስቲያኗን የእምነት መግለጫ እንጂ የቤተክርስቲያኗን ሥነ መለኮታዊ ትውፊት አይደለም። ይህ ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያን ታርክ ውስጥ ስንመለከት ነገረ ማርያም የተጀመረው ነገረ ክርስቶስን ለማብራራት ስለሆነ ሁለቱ አብረው የሚነሱ አስተምህሮዎች ናቸው።ስለዚህ የዚህ አስተምህሮ (የትምህርተ ማሪያም ) በትምህርተ ሥጋዌ ላይ ያለው ተጽዕኖው ወልድ የነሣው ሥጋን ምንነት በመግለጽ ይገለጣል። የክርስቶስ ኋጢአት የለሽ የመሆን ምክንያት እንደ ዘመኗ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ወልድ ከቅደስት ማርያም በነሣው ሥጋ እንጅ በእርሱ አምላክነት እና በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ላይ አይደደለም ማለት ነው።
ወንድም ሰለሞን “የወልድ ከማሪያም ሥጋን የመንሣቱ አስተምህሮ የእርሷን ንጽህና ለማወጅ እንዴት እንደ ተቀነባበረ ” እንዳሳይ ጠይቀውኛል። የእኔ አቋም እንድህ ይገለጻል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን (አሁን ያላቸው) ምሥጢረ ሥጋዌ እንዲህ ነው፦ ‹‹ ምስጢረ ሥጋዌ ከሦስቱ አካላት አንዱ፡- እግዚአብሔር ወልድ ከሰማያት ወርዶ ከቅድስት ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን፣ ከነፍስ ነፍስ ነሥቶ በሥጋ የመገለጹ፣ አምለክ ሰው፣ የመሆኑ ምሥጢር ነው፡፡ “ቃል ሥጋ ሆነ በእኛም አደረ›› (ዮሐ 1፡14)፡፡ . . . መለኮት ከሥጋ ሥጋ ከመለኮት ጋር ያለመለወጥ፣ ያለመቀላቀል፣ ያለ መለያየትና ያለ መከፋፈል በተዋሕዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆነ፡፡ ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ ሰውም ከሆነ በኋላ አንድ ወልድ አንድ ክርስቶስ ነው።” ከዚህ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት ያለው የቤተክርስቲያኗ የእምነት መግለጫ ሥጋ ስለ ተነሣበት ማርያም ማንነት ስገልጽ እንዲህ ይላል፦ ‹‹አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኀጢአት (ጥንተ አብሶ) ያላገኛት መርገመ ሥጋ ለፍስ የሌለባት ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ኀሊና ታስባ ትኖር ነበረች በሰው ልማድና ጠባይ ከሚደርሰውሥጋዊ አሳብና ፍቃድ ሁሉ የተጠበቀች ከተለዩ የተለየች ንጽሕት ቅድስት ቅዱሳን ናት፡፡ . . . እመቤታችን በውስት በአፍዎ በነፍስ በሥጋ ቅድስት ስለሆነች [አትኮሮት የሚሻ ቃል] እግዚአብሔር ለልጁ ማደርያ [ሥነ ሥጋዌ ቋንቋ ነው] መርጦታል፣ ማኀደረ መለኮት [ሥነ ሥጋዌ ቋንቋ ነው] እድትሆን አድርጓታል፡፡ አምላክን ለመውለድ [ሥነ ሥጋዌ ቋንቋ ነው] ያስመረጣትና ያበቃት ድንግልናዋ ንጽሕናዋ ነው፤ . . . ንጹሕ ነፍስ ንጹሕ ልቦና ለእመቤታችን ገንዘቦቿ ናቸው፡፡›› ይህ የቤተክርስቲያኗ የአሁን ዘመን የእምነት መግለጫ እንደሚያሳየን ትምህርተ ሥጋዌዋ ላለመለያት ከትምህርተ ማርያም ጋር ተጋብቷል። ስለዚህም አሁን ያለው የቤተክርስቲያኗ ክርስቶስ ትስብእት የመሆኑ ትምህርት ምስጥሩ ከቅደስት ማርያም ሥጋ በመንሣት አምላክ ሰው መሆኑ ላይ ነው። ሥጋ የነሣው እንደ ዘመኗ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አስተምህሮ ጥንተ አብሶ ከሌለባት ከቅደስት ድንግል ማርያም ነው። ከቅድስት ማርያም ሥጋን ነሣ ካልን (እኔም እንደማምነው እንዲሁም አንዳንድ የኦርቶዶክስ ሥነ መለኮት ምሁራንም እንደሚያምኑት ) ማርያም ሰው ነችና የሰው ልጆች ሁሉ ያለባቸው ጥንተ አብሶ ልኖርባት የተገባ ነው። እነርሱ (ቤተክርስቲያኗ) ግን በዘመኑ በኦፌሳላዊ መግለጫቸው ጥንተ አብሶ የለባትም ብለዋል። በባለፈው ጽሑፌ የእኔ መከራከርያ ነጥብ የነበረው ቤተክርስቲያኗ አሁን ያለት ምስጥረ ሥጋዌ አስተምህሮ መሰረት ያደረገው ከማርያም ንጹሕ ሥጋ (ጢአት የለሸ ሥጋ) መንሣቱ ላይ ነው። ክርስቶስ ከማርያም ጢአት የለሸ ሥጋ የመንሣቱ ምስጥር በአሁኑ የቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ መሠረት በእርሷ ንጽሑ መሆኗ ላይ እንጅ በእርሱ አምላክነት እና በመንፈስ ቅዱስ ስራ ላይ አይደለም። ለዚህ የቤተክርስቲያኗ የዘመኑ የማርያም ጥንተ አብሶት የሌሽነት አስተምህሮ ከቤተክርስቲያኗ የእምነት አባቶች አስተምህሮ እንደሚጻረር እማኝ ማቅረብ ይቻላል። “ቅዱስ ያሬድ፣ እመቤታችንና የድነታችን ምክንያት የሆነችው የአምላክ እናት ማርያም ከአዳም ሥር የተገኘች ናት። ነፍሷን አንጽተህ ልጅህን በርሳዋ እንዲያደር አደረግህ። (የጥር 21፡ዝማሬ)”
“ያማረ ኮከብ በማርያም አድረ
ሥጋዋን ሰአንጽቶ በማርያም አደረ
ርሷን ቀድሶ መለኮቱን ከሥጋዋ ጋራ አዋሐደ። (ነሐሴ 15 ቀን ዚቅ)”
“ያዕቆብ ዘሥሩግም፣ ከአብ የማይለይ ረጅም ፈትል ሳማይና ምድርን የፈጠርህ፣ በፍቃድህ ከሰማይ ወርደህ፣ የድንግል ማሕፀን ወሰነህ፣ የድች ልጅ ትንሽ ብላቴና አቀፈችህ፣ ነፍሷን አከበርህ፣ ሥጋዋንም አነጻሕ። አጸናሃትም አልደነገጠችም። (መ.ቅ. ቁጥር 21 ገጽ 438)” “ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ ቃል በግብረ መንፈስ ቅዱስ ሰው ሆነ የሚለውን ትርጓሜ ከሐድያንና መናፍቃን እንደሚያስቡት የመንፈስ ቅዱስ ሥጋ ኖሮት ወይም የተፈጠረ ሆኖ ሳይሆን፣ መንፈስ ቅዱስ የማርያምን ሥጋ አነጻ ቀደሰ፣ የአብ አካላዊ ቃልንም ለመፀነስ በቃች አደረጋት እንጂ ብሏል። (ሃይ፣ አበ. ገጽ. 125 ቁጥር 19)” ስለዚህ የወልድ ከቅደስት ድንግል ማርያም ንጹሕ ሥጋ የመንሣቱ የዘመኗ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትምህርት የማርያምን ንጽሕና የማስተማሪያ መሠረት ነው እላለሁ። ምክንያቱም “አምላክን ለመውለድ [ሥነ ሥጋዌ] ያስመረጣትና ያበቃት ድንግልናዋ ንጽሕናዋ ነው” የቤተክርስቲያኗ ኦፍሴላዊ የእምነት መግለጫ ይላልና። እንዲሁም መጋቢ ጥበብ ሰሎሞን የተባለ ሰው በውኑ ማሪያምን ማመን ይገባሃልን? በተባለ መጽሐፋቸው እንዲህ ብለዋል
“የቤተክርስቲያን ታርክ በምናጠናበት ወቅት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ያላስተማሩትን ትምህርት በተለይም በክርስቶስ ማንነት (በሚስጥረ ሥጋዌ ላይ) በየጊዜው ያነጣጠሩት ኑፋቄያት ተነስተው በወቅቱ ቤተክርስቲያን ትክክልና ቁርጥ መልስ ሰጥታለች። ለዚህ ለክርስቶስ ሰው መሆንና ማንነት(ለሚስጥረ ሥጋዊ) መልሷ (የትምህርት መነሻዋ) ደግሞ ከማሪያም ሥጋ መውሰዱ ሆኖ ስለማሪያም አጀንዳነት ግን በር ከፈተ።”. . . ይሁን እንጂ ሁሉም በዋናነት ክርክራቸው ስለክርስቶስ ሆኖ ማሪያም ሲሉም ከሰው ለማለት እንጂ ዛሬ እንደሚባለው ማርያም ጢአት ያሌለባት ስለመሆኗ፣ አማለጅ ለመሆኗ፣ ውዳሴና ስግደት ሊቀረብለት እንሚገባ ያስተማሩና የገለጹት አንዳችም የለም።”
ይህ ወንድማችን ባቀረበው ታርክ ማስረጃ እንደሚያሳየው ቤተክርስቲያኗ በክርስቶስ ሰው መሆን ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ክርስቶስ ከማሪያም ሥጋን እንደነሣ በማሳየት ምላሽ መስጠቷን ነገር ግን ይህ በዚህ በትክክለኛ መልኩ የተጀመረ የማርያም አሰተምህሮ ለሌላ (የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ለሌለው) የማርያም አስተምህሮ በር መክፈቱን፣ በመጨረሻም አሁን ወደ አለው የማሪያም ጢአት የሌሽነት ትምህርት ማደጉን እንመለከታለን። ይህ ሰው ከማርያም ሥጋ የይማኖት አባቶች ሲሉ ከሰው ማለታቸው እንጂ ያሁኗ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ እንደሆነው “ጥንተ አብሶ” ከሌላት ማርያም ማለታቸው አልነበረውም ይለናል። ይህ የቤተክርስቲያኗ የማኖት አባቶች አስተምህሮ ከጊዜ በሏ ተለውጦ አሁን ወደ አለበት የማርያም ጥንተ አብሶ የሌሽነት አስተምህሮ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህ እንዴት የወልድ ከማሪያም ሥጋን የመንሣቱ አስተምህሮ የእርሷን ንጽሕና ለማወጅ/ ለማስረዳት እንዴት እንደተቀነባበረ (አንድ ተዘጋጀ) መልስ አይሆንም ይሆን?
ሌላኛው ወንድማችን ሰለሞን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እምነት ነው ብሎ ያቀረበው የአትናቴዎስ የተባለው የቤተክርስቲያን አባት አስተምህሮው ነው። አስተምህሮውም “ሰዎች ሁሉ በጌታችን ሥጋ ድነትን አገኙ፤ ጌታችን የተዋሐደው ሥጋ እውነተኛ ነውና፤ ከእኛ ሥጋ ጋር አንድ ነውና እመቤታችንንም ቅደስት ድንግል ማርያም ወገናችን ናት፤ እኛ ሁላችን ከአዳም ተገኝተናልና። . . .” ነገር ግን ከሁለቱ ዮትኛው ነው የዘመኗ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫዬ ነው ብላ የሚትቀበለው? እኛም እንድንቀበለው የምነገደደው። ወንድማችን ሰለሞን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ የአትናቴዎስን ዓይነት ነው ብሎናል። ቤተክርስቲያኗ ደግሞ እምነት መግለጫዬ ነው ብላ ያስቀመጠችልን መረጃ አለ። የቤተክርስቲያኗ እምነት መግለጫ የሚለው “ከአዳም ዘር የተላለፈ ኀጢአት (ጥንተ አብሶ) ያላገኛት መርገመ ሥጋ ለነፍስ” ከሌለባት ከድንግል ቅድስት ማሪያም ሥጋን ነሣ ሲሆን፤ አትናቴዎስ የሚለው “ሰዎች ሁሉ በጌታችን ሥጋ ድነትን አገኙ፤ ጌታችን የተዋሐደው ሥጋ እውነተኛ ነውና፤ ከእኛ ሥጋ ጋር አንድ ነውና እመቤታችንንም ቅደስት ድንግል ማሪያም ወገናችን ናት፤ እኛ ሁላችን ከአዳም ተገኝተናልና።” ነው። እመቤታችን ከእኛ ወገን፤ እንደኛው ከአዳም ከተገኘት ጥነተ አብሶ አለባት ማለት ነው። ታዲያ ሁለቱ እርስ በእርሳቸው የሚቃረኑ ከሆነ ዬትኛውን የዘመኗ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫ አድርገን እንቀበል? የእኛ ነው ብለው ከቀረቡት መረጃ/ አስተምህሮ ውጭ ይህንን ነው የምታምኑት ብንል “ለቀባሪው ማርዳታችን” አይደል? ይህ እናቴ በልጅነቴ “ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው” ትለኝ የነበረውን ብሂል አስታወሰኝ።
በሁለተኛ ደረጃ የቤተክርስቲያንቷ (የዘመኗ) የትስብእት አስተምህሮ “የክርስቶስን እንደኛ ሰው መሆኑን ለማሳየት ሳይሆን ማሪያም ወላዲት . . . አምላክነት ለማሳመን የተቀነባበረ ትምህርት” መሆኑን በአለፈው ጽሑፌ የግርጌ ማስታወሻ ባቀረብኩት ሀሳብ ለይ የተሰነዘረ ሂስ ነው። የግርጌ ማስታወሻ ምንም እንኳ በጽሑፍ ውስጥ ለተጠቀሰው ሀሳብ እንደ ዋነኛ መከራከርያ ነጥብ መወሰድ ባይገባውም ምላሽ እንድሰጣቸው ስለጠየቁኝ እኔም በቅ ምላሽ መስጠት ይቻለኛል ብዬ ስላሰብኩ ለጥያቄአቸው እንዲህ ምላሽን ሰጥቻለሁ። የቤተክርስቲያኗን እምነት መግለጫ በትክክል በንጹሕ ሕሊና ላነበበ ሰው ይህንን አስተምሮ አያስተምርም ለማለት ይከብዳል። እንዲህ ይላልና “አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደችው [ሥነ ሥጋዌ ቋንቋ ነው] እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኀጢአት (ጥንተ አብሶ) ያላገኛት . . . እመቤታችን በውስት በአፍዎ በነፍስ በሥጋ ቅድስት ስለሆነች [ይህ አሰተውሎት የሚሻ ቃል ነው። የመመረጧን ሚክንያት ስለሚገልጽ] እግዚአብሔር ለልጁ ማደርያ [ሥነ ሥጋዌ ቋንቋ ነው] መርጦታል፣ ማኀደረ መለኮት [ሥነ ሥጋዌ ቋንቋ ነው] እድትሆን አድርጓታል፡፡” ይህ ዓረፍተ ነገር ምን ይላል? ፍርዱን ለእናንተ ትቼዋለሁ። “እመቤታችን ቅደስት ማሪያም” አምላክ- ሰው የሆነውን ክርስቶስን ወልዳለች። ይህ የሚያጋጨን አይመስለኝም። ነገር ግን በዘመኗ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫ እመቤታችንን መሠረት “ማደረ መለኮት”፣ ወላዲት አምላክ [ሥነ ሥጋዌ ቋንቋ ነው] እንድትሆን ያደረጋት ወይም ያስመረጣት “በውስት በአፍዎ በነፍስ በሥጋ ቅድስት” መሆኗ ነው ይለናል። ይህ በእርግጥ እኔ ያልኩትን አይልም? ከዚህ በተጨማሪይ አቶ አፈወርቅ ሀይሉ በድህረ ምረቃ መመረቅያ ጽሑፋቸው ላይ “ወላዲተ አምላክ ከሚለው የክብር ስሟ ጀርባ ያለው ሙሉ ሀሳብ ሥነ-ክርስቶሳዊ እንደ ሆነ እንመለከታለን” በማለት የእኔ (የቤተክርስቲያኗ የዘመኑ ሥነ ሥጋዌ እና ወላዲት አምላክ የሚለው ሀሳብ ግንኙነት አላችው የሚለውን የእኔን ሀሳብ) ይጋረል። ሀሳቡንም በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሰረተ እምነት ላይ በሰይፈ ስላሴ ከተጻፈ መጽሐፍ ዋቢ የሚሆኑ ሀሳቦችን በመውሰድ አስደግፎታል “ድንግል ማሪያም ወላዲት አምላክ ወይም እመ አምላክ (ሉቃ 1፡32) የተባለችው በድንግልና ከእርሷ የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ስለሆነ፤ ከእግዚአብሔር የተወለደው ከማሪያም ስለተወለደ ነው። ከእግዚአብሔር በመለኮታዊ ባህርይ የተወለደው በሰዋዊ ባህርይ ከማሪያም ስለተወለደ ነው። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ በሥጋ ከማሪያም ስለ ተወለደ እርሷ ወላዲት አምላክ ወይም እመ አምላክ ትባላለች። . . .” ይህ ነው እንግድ የቤተክርስቲያኗ የዘመኑ ትምህርተ ሥጋዌ ክርስቶስ እንደ እኛ ሰው መሆኑን ለማሳየት ሳይሆን ማሪያም ወላዲት አምላክ መሆኗ ለማሳመን የተቀነባበረ (የተዘጋጀ) ትምህርት ነው ያልኩበት ምክንያት።
በመጨረሻም የዛሬው ምክሬ የቤተክርስቲያናት የእምነት አቋም የሚለካው አሁን ባላቸው አቋም እንጅ ጥንት በነበራቸው አቋም አይደለም “በድሮ በሬ ያረሰ የለም”ና። በተለይ ወንድም ሰለሞን ያቀረበው የመከራከሪያ ሀሳብ መሠረቱ የቤተክርስቲያኗ የቀድሞ አቋም እንጅ የአሁን ስላልደል ምላሹ መሠረት የለውም እላለሁ። ምክንያቱም የአንድ ቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫ ትክክለኝነት የሚለካው አሁን በአለው አስተምህሮ ምንነት እንጂ ቀድሞ ምን ዓይነት አስተምህሮ ነበራት በሚል መስፈረት አይደለምና። ስለዚህም ቤተክርስቲያኗ አሁን ያለት የምስጥረ ሥጋዌ አስተምህሮ እግዚአብሔር ወልድ ጥንተ አብሶ ከሌለባት ከድንግል ማሪያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍን ነሥቷል ስለሚል ይህ ደግሞ ትክክል ስላይደለ ይህንን አስተምህሮ ለመቃረም ወደ እዚያኛው መንደር ስንሄድ በዚያኛው መንደር ያለውን አስተምህሮ አጥሮቶ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ፈትኖ፤ ትክክለኛውን ነገር ብቻ መውሰድ ይገባል እላለሁ። እንዲህ ያቀረብኩት ሀሳብ እንዴት ምልከታችን ያላጠራ “ጅምላ ጨራሽ መሣሪያን ማስወንጨፍ”፣ “ነጥሎ ያልመታ” እና “መካከለኛ ሀሳቦችን የሚያጎሳቁል” እንደሆነ ግልጽ አልሆነልኝም። የአውዳዊነት ስነ መለኮት መሠረቱ ሰዎችን በሚረዱበት ቋንቋ፣ ባሕል እና አስተሳሰብ ወንጌልን ማድረስ እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠውን እውነትን ማመቻመች አይደለም። ለዛሬው በዚሁ አበቃሁ።
ሚክያስ በላይ፣ የወልድ ሥጋ መንሣት የስርየታችን መሠረት ነው! ማቴቴስ መጽሔት ቁጥር 10 መጋቢት 2001 ዓም ገጽ 24
ሚክያስ በላይ፣ ክርስቶስ ወልድ ሥጋን ነስቷል! ማቴቴስ መጽሔት ቁጥር 8 ሐምሌ 2000ዓም ገጽ 27
ዚኒ ከማሁ ገጽ 12
ሰሎሞን አ. ገብረ መድን (ዘኦርቶዶክስ)፣ “ጅምላ ጨራሽ መሣሪያ” ማስወንጨፈፍ ቢቀርስ? ማቴቴስ መጽሔት ቁጥር 10 መጋቢት 2001 ገጽ 13
ተካልኝ ዱጉማ፣ “የሚክያስን ወልድ ሥጋን ነሥቷል”ን እንቀበል! ማቴቴስ መጽሔት ቁጥር 9 2001 ዓም
ሰሎሞን አ. ገብረ መድን (ዘኦርቶዶክስ)፣ “ጅምላ ጨራሽ መሣሪያ” ማስወንጨፈፍ ቢቀርስ? ማቴቴስ መጽሔት ቁጥር 10 መጋቢት 2001 ገጽ 35
ይህ የኦርቶዶክሳዊይን አፈር የሚያፈራው ሥነ መለኮታዉ ፍሬ ሁል ጊዜ አረም ነው የሚል አቋም ግን የለኝም። ግን በባለፈው ጽሑፌም ለማስጠንቀቅ እንደሞከርኩት “ሥነ-መለኮታዊ ቃላት እና ሀሳብን ስንጠቀም የሀሳብ ባለቤቶች ያንን ቃል ወይም ሀሳብ በምን ቅድመ እሳቤ እንደተጠቀሙበት መመልከቱ ከብዙ ስህተት ሊታደገን ስለሚችል ከመጻፋችን ወይም ከማስተማራችን በፊት የሰዎችን ሥነ-መለኮታዊ እሳቤ ምን እንደሆነ በጥንቃቄ ቢንመረምር ጥሩ ነው ስል ምክሬን በመለገስ አጠናቅቃለሁ፡፡” ተካልኝ ዱጉማ፣ “የሚክያስን ወልድ ሥጋን ነሥቷል”ን እንቀበልን! ማቴቴስ መጽሔት ቁጥር 9 2001 ዓም
አፈወርቅ ሃይሉ “A Survey of the Ethiopian Orthodox Church Mariology: An attempt to understand the origin, and Teaching Regarding Mary in the EOC” ገጽ 77-78
ዘኒ ከማሁ 78
ዚኒ ከማሁ ገጽ 84
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን እምንት፣ ሥረዓተ አምልኮና የውጭ ግንኙነት (ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፣ አዲስ አበባ፣ 1996) ገጽ 25-27
ዚኒ ከማሁ ገጽ 49 ይህንን ስል ግን በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በማሪያም ጥንተ አብሶ አልባነት ላይ ሁለት ዓይነት አመለካከቶች የሉም እያልኩ አይደለም። ቅደስት ማሪያም እንደኛው ሰው እንደሆነች ጥንተ እብሰት እንደለባት የሚያምኑ አሉ። ነገር ግን የቤተክርስቲያኗ የእምነት መግለጫ እንደሚያሳየን የአሁን ጊዜ የቤተክርስቲያኗ አቋም “ጥንተ አብሶት” የለባትም ይላል። አፈወርቅ ሃይሉ የተባለ ሰው “A Survey of the Ethiopian Ortodoox Church Mariology: An attempt to understand the origin, and Teaching Reagarding mary in the EOC” በተባለ ድህረ ምረቃ መመረቅያ ጽሑፉ ገጽ 106 ላይ “በብጹ ወቅዱስ አቡነ ጰውሎስ የሚመራው ቅዱስ ስኖድ በአለቃ አያሌው ( አሁን ያለው ቅዱስ ስኖድ ተቃዋም) እና እንደ ማህበረ ቅዱሳን ያሉ የተራ ምዕመናን የማህበር እንቅስቃሴዎች ተጽዕኖ ምክንያት ይህ አመለካከት [የማሪያም ጥንተ አብሶ የሌሽነት ትምህርት] የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኦፊሴላዊ መግለጫ እንድሆን ወስነዋል።” ብሏል። ትርጉም ከራሴ
ዚኒ ከማሁ ገጽ 114 “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ትምህርተ ማሪያን ከሌሎች እንደ የአሌክሳንድሪያ ኮፕትክ ቤተክርስቲያን እና የግሪክ ኦርቶዶክ ቤተክርስቲያን ኦርቶዶክሳዊ ትውፍት በሆነው ለማሪያም አክብሮትን መስጠት እና የአማላጅነት የመሆኗ እምነታቸው/አስተምህሮአቸው ይመሳሰላሉ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንዲሁም ከሮም ካቶልክ ቤተክርስቲያን ትውፍት ጋር ማሪያም ጥንተ አብሶ የለባትም በሚለው ትምህርት ትመሳሰላለች።” ትርጉም ከራሴ
ተቀነባበረ ማለት ትርጓሜው ምንም እንኳ በአሉታዊ መልኩ አንድን ሰው ሳያውቅ በማታለል የምፈጸምን ነገር የሚያመልከት ቢሆንም ትርጓሜው ይህ ብቻ ሳይሆነ አንድን ነገር ሰዎች በሚረዱት መልኩ ማዘጋጀትንም የምያመልከት ጭምር በመሆኑ እኔም በጽሑፌ ውስጥ አቀነባበሩ ስል ሸወዱን ወይም አታለሉን ማለት ፍለጌ ሳይሆነ እንዴት ሐሳባቸውን ለማስደገፍ አዘጋጁት/አቀናጁት ለማለት ስለሆነ እንድህ ብረዱኝ።
ሰሎሞን አ. ገብረ መድን (ዘኦርቶዶክስ)፣ “ጅምላ ጨራሽ መሣሪያ” ማስወንጨፈፍ ቢቀርስ? ማቴቴስ መጽሔት ቁጥር 10 መጋቢት 2001 ገጽ 34
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን እምንት፣ ሥረዓተ አምልኮና የውጭ ግንኙነት (ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፣ አዲስ አበባ፣ 1996) ገጽ 25-27 የዘመኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ሥጋዌ ከትምህርተ ማሪያም ጋር ላለመፋታት የተጋባ ነው። ምክንያቱም አስተምህሮአቸው ወልድ ሥጋን የነሣው የጢአት እብሰት ከሌለባት ከቅደስት ማሪያም ስለሆነ ትምህርተ ሥጋዌአቸውን ከትምህርተ ማሪያም ነጥለን መመልከት አንችልም። በደንብ እንድታይ ያደመቅሁት እና ሀሳቡን በደንብ ይገልጽልኝ ዘንድ በቅንፍ ውስጥ ያስቀመጥኩት እኔ ነኝ።
ዚኒ ከማሁ ገጽ 49
አፈወርቅ ሀይሉ ገጽ 105
ዓለማየሁ ሞገስ፣ ሁሉም ይወቅ ገጽ 158
ዚኒ ከማሁ
ዚኒ ከማሁ
ዚኒ ከማሁ
መጋቤ ጥበብ ሰሎሞን ፤ በውኑ በማሪያም ማመን ይገባሃልን? 2000 ዓም ገጽ 167-168 የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ እንዴ ከወንጌላዊያን አማኞች ወገን ሳይሆን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ወገን ነው።
ሰሎሞን አ. ገብረ መድን (ዘኦርቶዶክስ)፣ “ጅምላ ጨራሽ መሣሪያ” ማስወንጨፈፍ ቢቀርስ? ማቴቴስ መጽሔት ቁጥር 10 መጋቢት 2001 ገጽ 34 ምንም እንኳ ይህ ሰለሞን የጠቀሰው ክፍል እንዴት አድረጎ የዘመኗን የአርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫ መሆን እንደሚችል ባይታየኝም። ምክንያት፤ የአትናቴዎስ አስተምህሮ ከአሁኗ የቤተክርስቲያንቷ አቋም ጋር ይጋጫልና።
ዚኒ ከማሁ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን እምንት፣ ሥረዓተ አምልኮና የውጭ ግንኙነት (ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፣ አዲስ አበባ፣ 1996)
አፈወርቅ ሃይሉ “A Survey of the Ethiopian Orthodox Church Mariology: An attempt to understand the origin, and Teaching Regarding Mary in the EOC” 103
ዘኒ ከማሁ ገጽ 104 አፈወርቅ ሀይሉ እንደጠቀሰው። ትርጉም ከራሴ Seife Selassie, ye-Ethiopia Oryhodox Tewahedo Bete Kristian Meserete Haimanot (Addis Ababa: Tensae Ze- Gubae Printing Press, 1982 EC), 29-30
ማመቻመች ያልኩበት ምክንያት እዚያ ሰፈር አለ የተባለው “ትክክለኛ” ትምህርተ ሥጋዌ “ድሮ” እንጂ አሁን ስለተበረዘ/ከትምህርተ ማሪያም ጋር ስለ ተቀየጠ ለአዊዳዊነት ይጠቅማል በተባለ፤ ለመካከለኛነት (ለመግባቢያነት) ይጠቅማል በሚል ስም ሰዎችን ኦርቶዶክሳዊያን በዚህ ረገድ ልክ ናቸው እያልን ወደ ቅይጣዊነት እንዳንመራ ስለፈራሁ በአሁን ወቅት ያላቸወን አስተምህሮ ለይቼ ለማሳየት ያክል ነው።

Comments
Post a Comment