በስሜ ብትለምኑ
“በስሜ ብትለምኑ”
በተካልኝ ዱጉማ
በዘመናት መካከል የተለመደው የጸሎት መዚጊያ የሆነው ሀረግ “ይህንን በልጅህ ስም ጠየቅን”፣ “በኢየሱስ ስም ስንል ጸለይን”፣ “በስምህ ጸለይን” ወዘተ ታሳቢ ያደረገው የመጽሐፍ ቀዱስ ክፍል ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14 እና 15ን ነው። ይህንንም ክፍል ሳጠና ስለ ክፍሉ ያለን መረዳት ከጸሎት ማሳረግያነት ያልበለጠ መሆኑ ተሰማኝ። በእርግጥ ኢየሱስ በዚህ ክፍል ውስጥ “በስሜ ብትለምኑ” ደቀ መዛሙርቱን ሲላቸው በጸሎታቸው ማሳረግያ ላይ “በኢየሱስ ስም እንለምናለን” የሚለውን ሀረግ እንድጠቀሙ ፈልጎ ይሆንን ወይስ ይህ “በስሜ ብትለምኑ” የሚለው ሀረግ ሌላ ጥልቅ ትርጉም ይኖረው ይሆን? ብዬ እራሴን ጠየቅኩ። ክርስትና በራሱ በጥያቄዎች የተሞላ አይደል? ዕለት ተዕለት ጥያቄዎችን ለመመለስ እና እውነትን ለመረዳት ደግሞም የተረዱትን እውነት ለመኖር የሚደረግ ትንቅንቅ። ይህንን የኔን ስጋት የተጋሩ አንድ ኮንስታበል የተባሉ የመጸሐፍ ቅዱስ ምሁር እንዲህ አሉ “ብዙኑ ክርስቲያኖች ስለዚህ ክፍል ያላቸው አመለካከት ጥያቄዎቻቸውን በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ካቀረቡ በላ በስተመጨረሻ ይህን በኢየሱስ ስም ጠየቅን የሚለውን ሀረግ መጨመር ይመስላቸዋል” ብለዋል። እኔም ወደ አእምሮዬ የመጣውን “በስሜ ብትለምኑ” የሚለውን ሀረግ ትርጉም ምንነት ከጸሎት ማሳረግያነት የዘለለ ትረጉም ሊኖረው ይችል ይሆንን ለሚለው ጥያቄ በዮሐንስ 14 እና 15 ውስጥ በሚገኘው ሀረግ ላይ ባደረግሁት ጥናት ያገኘሁትን፣ የተረዳሁትን እና የማምንበትን በዚች አጭር መጣጥፍ ለእናንተ ላካፍል ወደድኩ። በዚህም ጽሑፍ በመጀመሪያ ይህ ሀረግ ስለሚገኝበት አውድ ትንሽ ትንታኔ እሰጣለሁ። በሁለተኛ ደረጃ የ”ስሙ” ትርጉም ምን እንደሆነ እገልጻለሁ። በመቀጠልም በዚህ ስም መጸለይ ምን ማለት እንደሆነ አሳያለሁ። በመጨረሻም በዚህ ስም መጸለይ ከእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድ አንጻር ስላለው ጠቀሜታ በማሳየት አጠናቅቃለሁ።
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የፋሲካ በዓልን አክብረው በጨረሱበት እንዲሁም አስቆሮቱ ይሁዳ ከደቀ መዛሙርቱ በመለየት ኢየሱስን አሳልፎ ሊሰጥ በሄደበት ወቅት ነበር ኢየሱስ የመሰናበቻ ንግግሩን የጀመረው። ከኢየሱስ ጋር በነበራቸው የዓመታት ቆይታ የተነሳ በገበታው ዙርያ ያላቸውን ሁኔታ የተመለከተ ሰው እርስ በእርሳቸው የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው አይጠራጠርም። ኢየሱስ በዚያ ዕለት ከዚያ ቀን በፊት ደቀ መዛሙርቱ ሰምተው የማያውቋቸውን ብዙ ነገሮችን አስተምሮአቸዋል። እርስ በርሳችው እንድዋደዱ፣ እርሱ ለእነርሱ ቦታን ልያዘጋጅ እንደሚሄድ፣ እርሱ የእግዚአብሔር መገለጥ እንደሆነና የእግዚአብሔርን ትክክለኛ ማንነት የሚያሳይ መሆኑንም ነግሯቸዋል። ወደ ፊት ሊፈጽሙት ስለሚገባው እንዲሁም ስለ ተሰጣቸው ተልዕኮም አሳይቷቸዋል። ከኢየሱስ የዚያን ቀን ንግግር ውስጥ የመልዕክቱን እና የተልዕኮውን ከባድነት የሚያመላክት ነገርን እንመለከታለን (ዮሐንስ 14፡ 12-14 ይመልከቱ)። ደቀ መዛሙርቱ እስከ እዚህ ሰዓት ድረስ በስሙ ምንም ነገር ለምነው ስለማያውቁ ይህ ለእነርሱ አዲስ ትዕዛዝ፣ አዲስ መገለጥ ነው፤ ምክንያቱም እርሱን ይወክሉት ዘንድ ገና አልሾማቸውምና፤ እርሱ ይሰራ የነበረውን ነገር መስራት ገና አልጀመሩም ነበር።
1. የ”ስሙ” ትርጉም
ደቀ መዛሙርቱ ጌታቸውን የሚያውቁት ኢየሱስ በሚለው ስሙ ነው። የስሙ ትርጓሜም አዳኝ ማለት ነው። ክርስቶስ የሚለው ስም ንጉሥነቱን፣ ጌታ የሚለው ስም አምላክነቱን እና ዘላለማዊነቱን እንደሚያሳይ ሁሉ ኢየሱስ የሚለው ስም የእርሱን የደንነት ሥራ ያሳያል። ሰዎችን ከጢአት እስራት ነጻ መውጫ መንገድ ያዘጋጀበትን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ሰዎችን ያስታረቀበትን ማለት ነው። ይህ ስም ነው ክርስቶስን ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያደረገውም። ስለዚህ ነገር የፊልጵስዩስ መልዕክት ጸሐፊ ሲናገር ፊልጵስዮስ 2፡9-11 “ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ . . . በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥” ነው። ሰዎች ሁሉ የክርስቶስን ንጉስነት እና ጌትነትን በተረዱ ቁጥር ስግደትን ሲሰጡ መመልከት ለአዲስ ኪዳን አንባቢ እንግዳ ነገር አይደለም። ምክንያቱም እግዚአብሔር ከስልጣን ሁሉ በላይ ስልጣን ለእርሱ ሰለ ሰጠው ነው። የዚህ መጣጥፍ ትኩረት “ስሜ” የሚለው ቃል ነው። ከዚህም በላይ ደቀ መዛሙርቱም በዚህ ስም ይል ታአምራትን ማድርጋቸውንም ልንዘነጋ አይገባም። ታዲያ ይህ “ስሜ” የሚለው ቃል ትርጉም ምን ይሆን?
በዮሐንስ 14 እና 15 ውስጥ የሚገኘውን “በስሜ” የሚለውን ቃል ለመረዳት በዕለት ተዕለት ህይወታችን የምናደርጋቸውን ነገሮች መመልከት አስፈላጊ ይመስለኛል። አንድ ሰው በሌላኛ ሰው ስም አንድ ነገርን ሲያደርግ ይህ ድርጊት የሚያመለክተው ሰውዬው በስሙ ከሚያደርግለት ሰው ጋር ያለውን ህብረት/ግንኙነት ነው። ነገር ግን ይህ ህብረት የተለያየ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም ሕጋዊ፤ የዝምድና ወይም የፍቅር ግንኙነት የሚባሉ የመወከያ/የእንደራሴ ማደውጊያ መንገዶች አሉና። ሕጋዊ የምንለው ግንኙነት በዕለት ተዕለት ህይወታችን የተለመደውን በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ሰዎች በሚኖራቸው ሕጋዊ ትስስር፤ አንዱ በሌላኛው ሰው ሰም ጉዳይን ለመፈጸም የሚያስችለውን ነው። እንዲሁም አንድ የንግድ እንቅስቃሴን የሚመራ የአንድ ድርጅት ተቀጣሪ ሁል ግዜ በቀጣሪው ስም ጉዳዮችን ያስፈጽማል። ቀጣሪው እስከ ሰጠው ስልጣን ድረስ በመጠቀም ይገዛል፣ ይሸጣል እንዲሁም ውል ይዋዋላል። ሁለተኛው ዓይነት ህብረት ልጅ ከአባቱ ጋር ያለው ትስስር ነው። ልጅ የአባቱን ስም ይሸከማል፤ አባቱን ይወክላል። የአባቱን ስም ስለሚይዝም ይህ ስም ለእርሱ የሚያስገኝለት ጠቀሜታ እንዲሁም ከእርሱ የሚጠበቅበት ነገር መኖሩ እሙን ነው። ሦስተኛው በፍቅር የሚሆን ትስስር ነው። ይህ በትዳር ውስጥ የሚገለጥ ነው። ምንም እንኳ በሀገራችን አንድት ሴት የባለቤቷን ስም ባትወስድም ነገር ግን “የእጌሌ” ባለቤት መባሏ ግን የማይቀር ነገር ነው። ይህ ከዕለት ተዕለት ኑሮአችን የወሰድኩት ምሳሌ በከፊሉም ቢሆን የ”ስምን” ጠቀሜታ የሚያሳይ ቢሆንም “በስሜ” የሚለው ቃል ትርጉም ከእነዚህ ሕጋዊ (በውክልና)፤ የዝምድና (በደም ትስስር) እና የፍቅር (በጋብቻ) ግንኙነትን ከማሳየት የበለጠ ትርጉም አለው።
ስሙ የሚወክለው እሱን ነው። የእኛ በስሙ መጸለያችን ወይም ነገሮችን መከወናችን የሚያሳየው እኛ ከእርሱ ጋር ባለን ትስስር ያገኘነውን ስልጣን ነው። “በኢየሱስ ስም መጸለይ ማለት እንደ ኢየሱስ ወኪል ሆኖ በአብ ፊት በጸሎት መቅረብ” መሆኑን ኮንስታብል ይገልጻሉ። ሌላ አንድ የመጸሐፍ ቅዱስ ምሁር ከዚህ ሀሳብ ጋር በመስማማት “በዚህ አውድ ‘ስሜ’ የሚለው ቃል ትርጉም ይህንን ይመስላል፦ የእርሱን ክብር የሚፈልጉ እና ስለ እርሱ በትክክል የሚናገሩ እንዲሁም የእርሱ እውነተኛ ስልጣን የተሰጣቸው ወኪሎቹ ናቸው።” በማለት ገልጸዋል። እርሱ የወከላቸው፤ ተልዕኮ እና ስልጣን የሰጣቸው እንደራሴዎቹ ማለት አይደል?
2. በስሙ መጸለይ ማለት ምን ማለት ነው?
የጸሎት ሕይወታችን መሠረት የሚሆነው ከክርስቶስ ጋር ያለን ህብረት ነው። በመጀመሪያ ይህ የሚያሳየን ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት ያለንን ቦታ ነው። ከኢየሱስ ጋር በአንድም በሌላም መንገድ ህብረትን ፈጥረናል። እኛ የእርሱ አጋሮች፤ አገልጋዬቹ ነን። የምንሠራው በስሙ ነው፤ በተሰጠን ውክልና እና ተልዕኮ ማለት ነው። ከእርሱ በተሰጠን ስልጣን ነው ነገሮችን የምንከውነው። ይህ ስልጣን በደንነት እና ዳግም ውለደት ያገኘነው አዲስ ስፍራ ነው። የተሰጠንን ተልዕኮ የምንፈጽመው በስሙ ነው። ኢየሱስ የሚለው ስም እንደሚያመለክተው የእርሱ ተልዕኮ የነበረው ሰዎችን ማዳን ሲሆን ለእኛ ይህንን ተልዕኮ እንፈጽም ዘንድ ውክልና እና አደራ ተሰጥቶናል። የኢየሱስ ተልዕኮ የነበረው አብን ማክበር ሲሆን እኛ ከኢየሱስ የተቀበልነው ተልዕኮ እና የውክልና ስራ ኢየሱስ የጀመረውን አብን የማክበር ስራን ነው። ኢየሱስ ይህንን በዮሐንስ 14፡ 12 ገልጾታል። ከዚህ የእርሱ ቃል በስሙ የመጸለያችን ጠቀሜታውም ኢየሱስ የሰራውን ለእኛም በውክልና የተሰጠንን አደራ ለመወጣት አስፈላጊ መሆኑን እንገነዘባለን።
ወካይ የሚለው ቃል ትርጉም ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃለት እንዲህ ይፈታዋል “ወከለ፤ (ወክሎ፡ ወከለ)፤ አመነ፡ ተካ፤ ወኪል፡ ተጠሪ፡ ቶፋ አደረገ፡ ጥፋቱም፡ ጥፋቴ፡ ልማቱም፡ ልማቴ፡ ብሎ።” ይላል። እንዲሁም ተወካይ ለሚለው ቃል ይህ መዝገበ ቃለት ይህንን ፍች ይሰጠዋል “ተወከለ፡ ታመነ፡ ተተካ፡ ምትክ፡ ኾነ፤ በሰዉ ፋንታ፡ ሠራ።” እንዲሁም የአለቃ ኪዳነ ወልድ ስዋሰው ወግስ መዝገበ ቃላት ዐዲስ እንዲህ ይላል “ተወከለ፤ በቁሙ፤ ወኪል ሆነ፤ ታመነ፤ ለሿሚው፤ ለወካዩ። አመነ፡ ማመን፡ እምነቱን ጣለ፡ በመወከል፤ ተስፋ አደረገ፤ ወካዩ፡ ወኪሉን። ታመነ፡ ማለት፡ ባማርኛ፡ እንደ፡ ሳቢ፡ ዘር፡ ነው፤ ሁለት፡ ያሳያል፡ ለሌላ፡ መታመንንና፡ በሌላ፡ ማመንን።” እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ነገሮችን (ወኪሎቹ መሆናቸውን)፤ በእርሱ የተወከሉ፤ እርሱን የሚወክሉ መሆናችውን ታሳቢ በማድረግ ነው ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ “በስሙ” እንዲጠይቁ ያዘዛቸው። ማለትም ያለንን ቤተሰባዊ ትስስር እና የተለዕኮአቸውን አንድነት ታሳብ በማድረግ እንዲህ አላቸው “እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና አብም ስለ ወልድ እንዲከብር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። 14ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።” (ዮሐንስ 14፡13-14 የ1954 ትርጉም)። እንደ ደቀመዛሙርቱ ሁሉ ተልዕኮአችን አንድ እና አንድ ነው እርሱም እርሱ ስሰራ የነበረውን ነገር መስራት። ኢየሱስ በምድር ላይ በተመላለሰበት ወቅት አብን በነገሩ ሁሉ እንዳከበረ ከእኛ የሚጠበቀው ይሄንኑ እንድንፈጽም ነው። "በስሙ ስንጸልይ የእርሱ ሰራተኞች መሆናችንን እየመሰከርን ነው። በዚህ መንገድ የሚጸልይ ሰው የሚጠይቀው እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ነው ወይም የሚጠይቀው በእግዚአብሔር ፍቃድ ጥላ ስር ያለን ነገር ነው ምክንያቱም ኢየሱስ (ወካዩ) በምድር ላይ ሲመላለስ አባቱን ይጠይቀው የነበረው እንደዚያ ስለነበር ነው። “በኢየሱስ ስም ጸልዮ” ከእግዚአብሔር ፍቃድ ውጭ መጠየቅ የማይታሰብ እና እርስ በእርሱ የሚቃረን ነገር ነው” ምክንያቱም በኢየሱስ ስም መጸለይ ማለት እንደ ፍቃዱ መጸለይ ማለት ስለሆነ። ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር ሲናገሩ “በኢየሱስ ስም መጸለይ ማለት ከኢየሱስ ጋር በአካል እና በዓላማ በመዋሃድ መጸለይ ማለት ነው። ምክንያቱም የአንድ ሰው ስም የሚያመለክተው የእርሱን ባሕርይ እና ግብ ስለሆነ ነው።” ምንም እንኳ ከላይ ያነሳቸው በመዳናችን የምናገኘው ኢየሱስን በምድር ላይ መወከል እና በእግዚአብሔር ፊት ያለን ስፍራ እና ህብረት መሰረታዊ ቢሆኑም ከዚህ በላይ ግን ከጸሎታችን ጋር ቀጥታ ተዛማጅነት ያለው ቅድመ ሁኔታዎች አሉ። በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14 እና 15 ሀተታ ውስጥ ኢየሱስ በስሙ እንዲለምኑ ከገለጸበት ቦታ በመቀጠል ያለውን ስንመለከት እንዲህ የሚል ነገር እናያለን “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ”። ኢየሱስ የነገራቸው ነገር የእኔ እውነተኛ ወኪሎቼ ከሆናቸሁ፣ የእኔ እውነተኛ አገልጋዮች ከሆናች፣ እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆናችሁ እና እውነተኛ የክርስቶስ ሙሽራ ከሆናችሁ ትእዛዜን ጠብቁ። ይህ ዝምድናችን የእውነት ከሆነ ትዕዛዜን ጠብቁ ማለት አይደል? በስሙ ለመጸለይ፣ እንደ እውነተኛ ወኪሎች ለመጸለይ፣ እንደ እርሱ ፍቃድ ለመጸለይ ይህ ቅድመ ሁኔታ አስፈላጊ ነው። መታዘዝ በስሙ የመጸለይ አንዱ አካል ነው። ይህ ማለት ግን በራስ ጥረት የእግዚአብሔርን ፍቃድ ለመፈጸም ወይም መልካም ስራን ለማድረግ የሚደረግ ጥረት አይደለም። ከኢየሱስ ንግግር የምንረዳው በ “ስሜ ጸልዩ” ከሚለው ለአማኞች ከተሰጠው የጸሎት ቅድመ ሁኔታ (ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ) ጋር ተያያዥነት ያለው ነገር የሚገኘው ከመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት እና ከክርስቶስ ጋር በመጣበቅ ላይ ነው። እነዚህ ሁኔታዎች እርስ በእርሳቸው የተቆራኙ ናቸው።
በስሙ ለመጸለይ ቅድመ ሁኔታ ሆኖ የተቀመጠውን መታዘዝን ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ከገለጸላቸው በላ በቀጥታ ያመራው ወደ መንፈስ ቅዱስ የመምጣት የተስፋ ቃል ነው። የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት እርሱን የማገልገላቸው፣ የመታዘዛቸው እና በስሙ የመጸለያቸው ቁልፍ ነገር ነው። ምንም እንኳ የመንፈስ ቅዱስን አጠቃላይ አገልግሎት በዚህ ጽሑፌ ለመዳሰስ ባልሞክርም ከዚህ ጽሁፍ ጋር ተዛማጅነት ያለውን መንፈስ ቅዱስ ለአማኞች ያለውን አገልግሎት “በመንፈስ ቅዱስ መሞላትን” ለማየት እሞክራለሁ። በሐዋርያት ስራ ውስጥ ደቀ መዛሙርቱ በተከታታይ በመንፈስ ቅዱስ ይሞሉ ነበር። ይህ ደግሞ ለመንፈሳዊ ህይወታቸው በጣም አስፈላጊ ነገር ነበር። አንድ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ተሞላ የሚባለው መንፈስ ቅዱስ የአማኙን ሕይወት ሲቆጣጠር፣ በሕይወቱ ላይ ገዥ ሲሆን ማለት ነው። መንፈስ ቅዱስን ዕለት ዕለት መሞላት የወካዩን ፍቃድ ለማወቅ አስፈላግ ነገር ነው። ሰዎች ሕይወታቸው በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር በሚሆንበት ወቅት ሀሳባቸው እና ሕልማቸው ሁሉ እግዚአብሔርን ማክበር እና እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ መኖር ብቻ ይሆናል። ይህንን አብን የማክበር ስራን ኢየሱስ በምድር ላይ ፈጽሞታል። እኛም እንፈጽመው ዘንድ ውክልና እና ተልዕኮ ተሰጥቶናል። ውክልናችን ግን እንዲሁ በራሳችን ጥረት የምንወጣው ሳይሆን በተሰጠን የመንፈስ ቅዱስ ይል የሚፈጸም ነው። በመንፈስ ቅዱስ ይል ዕለት ዕለት ብንሞላ፤ በእርሱ ህልወት ውስጥ ዘወትር ብንኖር፤ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ እንኖራለን፤ እንጠይቅማለን።
በኢየሱስ ስም የመጸለይ አካል የሆነው ሌላኘው ክፍል “በእርሱ መኖር” የሚለው ነው። በዮሐንስ 15 ላይ ኢየሱስ በእርሱና በደቀ መዛሙርቱ መካካል ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ አንድ ምሳሌን ተጠቅሟል። በመጀመሪያው ቁጥር ኢየሱስ እራሱን ፍሬ ከማታፈራው እስራኤል ጋር በማነጻጸር ፍሬአማዋ “እውነተኛ የወይን ግንድ” እኔ ነኝ ብሏል። በዚሁ ምዕራፍ ውስጥ ቁጥር 15 ላይ የእርሱን የወይን ግንድነት እና የደቀመዛሙርቱን “ቅርንጫፍ”ነት እውነታን ገልጿል። ይህ ምሳሌ ለደቀ መዛሙርቱ ግልጽ ነው። ፍሬያማ ካልሆነችው የወይን ግንድ ከእስራኤል ተቆርጠው ከእውነተኛው ግንድ ጋር ተጣብቀዋል። ቅርንጫፍ ከግንዱ ተላቆ ፍሬ ማፍራት ስለማይችል ስለዚህም እናንተም ፍሬ ማፍራት ከፈለጋችሁ ይላቸዋል ኢየሱስ በቁጥር 4 ላይ “በእኔ ኑሩ እኔም በእንናተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም።” የኢየሱስ ምክንያታዊ ገለጻ ግልጽ ነበር። የእነርሱ ፍሬያማነት መሰረት የሚሆነው ከእርሱ ጋር ያላቸው ህብረት እና ጥምረት ላይ ነው። ከኢየሱስ “በእኔ ነሩ” ከሚለው ትዕዛዝ የምንረዳው ደቀ መዛሙርቱም ይሁን ሁሉም አማኞች በጸጋው በእግዚአብሔር ፊት የሚያገኙት ነገር ሳይሆን የራሱ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች ያሉት ነው። ለፍሬያማነት እና ለውጤታማ ጸሎት፣ እውነተኛ የኢየሱስ ወኪል ሆኖ ለመኖር ከእውነተኛው የወይን ግንድ ጋር መጣበቅ አስፈላጊ ነው። በእግዚአብሔር ፊት የሚኖረን ስፍራ ብቻ ሳይሆን በእርሱ ለመኖር ያለን ፍላጎት ወሳኝነት አለው።
በምዕራፍ 15 ቁጥር 7 ላይ በኢየሱስ ስም ከመጸለይ ጋር ከፍተኛ ተዛመጅነት ያለውን ሀሳብ እናገኛለን። ይህ ሌላኛው በስሙ ከመጸለይ ጋር ትይዩ የሆነ ቅድመ ሁኔታዎች ያሉት የተስፋ ቃል ነው። “በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።” ይህ ቅድመ ሁኔታ ሁለት ክፍሎች አሉት። የመጀመሪያው በእርሱ መኖር ሲሆን ይህም የሚያሳየን የህልውናችን መሰረት ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ነው። ከእርሱ ጋር ህያው የሆነ ውህደት ቢኖረን የሚገባውንም ፍሬ እንደምናፈራ ያሳያል። ሁለተኛው የጸሎት ቅድመ ሁኔታ “ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ” የሚል ነው። የህልውናችን መሰረት ብቻ ሳይሆን ቁጥር 2 እና 3 እንደሚያሳየው ቃሉ ወይኑን ያጠራዋል ፍሬ የማያፈራውንም ያስወግደዋል። የእግዚአብሔር ቃል በውስጣችን ሲያድር ብቻ ነው እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ እንዲሁም እንደተሰጠን ዓላማ መጸለይ፣ ክፉውን ከመልካሙ መለየት እና እንደ እውነተኛ ወኪሎች የእግዚአብሔርን ፍቃድ በማወቅ መጸለይ የምንችለው። ይህንን ማድረግ የምንችለው በመንፈስ ቅዱስ ዕለት ዕለት የምንሞላ ከሆነ ብቻ ነው። የተስፋ ቃሉም “በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።" ይህ በግልጽ “በስሜ ለምኑ” ከሚለው ሀረግ ጋር ይመሳሰላል። አንዱ ሌላኛውን እንድንረዳ ያደረጋል።
3. በዚህ ስም መጸለይ ከእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድ አንጻር ያለው ጠቀሜታ
የእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድ ከሰዎች ጋር ህብረት ማድረግ ነው። ይህም ህብረት በመጀመሪያ አዳም በሰራው ጢአት ምክንያት ተበላሸ። ይህንንም የተበላሸ ሁኔታን ለማስተካከል ኢየሱስ ወደዚች ምድር መጥቷል። ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቁበትን መንገድ አዘጋጅቷል። ኢየሱስ የሚለው ስም የሚያመለክተው እርሱ ሊፈጽመው የመጣውን ተልዕኮ ነው፤ ሰዎችን ከጢአት እስራት ነጻ ማውጣት። ለእኛም በውክልና የተሰጠን ተልዕኮ ይህ ነው። ሌላም አይደለም ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ፣ ከጢአት እስራት ነጻ ውጡ የሚል ነው። እንደ እውነተኛ ተወካይ ለመኖር እና ለመጸለይ የእውነተኛ ተወካይ ባህሪ ሊኖረን ግን የግድ ነው። ይህም የሚቻለው በእርሱ እገዛ ብቻ ነው። የኢየሱስም እገዛው የሚገኝበትን፤ መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክላቸው ቃል ገብቶአል። ስለዚህም ዘላለማዊውን የእግዚአብሔርን እቅድ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንድያደርጉ እስከ ሆነ ድረስ እኛም የተሰጠንን ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት፤ ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ለማለት፤ በመጀመሪያ እኛ እራሳችን ትክክለኛ ወኪል ሆንን መቅረብ አለብን። ለተልዕኮው ውጤታማነት የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ ለመጠየቅ በመጀመሪያ ትክክለኛ ሆኖ መገኘት፤ ታማኝ ወኪል ሆኖ መገኛት ያስፈልጋል። ይህ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ እና በስሙ መጸለይ መካከል ያለውን ግንኙነት ግልጽ ያደርገዋል። ምክንያቱ እንዲህ ነው የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ ከሰዎች ጋር ህብረት ማድረግ ሲሆን ይህም በጢአት ምክንያት ተበላሽቷል። ለእኛ የተሰጠን ተልዕኮ ሰዎችን ከጢአት እስራት ነጻ የሚወጡበትን መንገድ ማሳየት እና ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት ህብረት እንደምያደርጉ ማመላከት ነው። ይህንን ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት የሚያያስፈልገን እውነተኛ ወኪል ሆኖ መገኘት ነው። እውነተኛ ወኪል ለመሆን የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ያስፈልገናል። እርሱም ተሰጥቶናል። ዕለት ዕለት በመንፈስ ቅዱስ ብንሞላ፤ በእርሱ ህልውና እና መገኘት ውስጥ ብንኖር፤ ጸሎታችን እንደ እኛ ፍላጎት እና ፍቃድ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድ ይሆናል፤ የምንጸልየው እንደ ትክክለኛ ወኪሎች ይሆናል።
4. ማጠቃለያ
በአጠቃላይ ኢየሱስ በስሜ ጸልዩ ሲላቸው ሊላቸው የወደደው ነገር በእውነት በእኔ ስም፤ እንደ ትክክለኛ ወኪሎቼ ጸልዩ ማለቱ ነበር። ለዚህ ግን እውነተኛ ወኪል ሆኖ መገኘትን እንደ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጧል። እውነተኛ ወኪል የመሆን መስፈርቱ እርሱን መውደድ ነው። መውደድ ግን በአፍ የሚነገር የቃላት ድርደራ ሳይሆን በተግባር የሚገለጥ ነገር ነው። ትዕዛዙን መጠበቅ። ትዕዛዙን ለመጠበቅ ግን የሚያስችል ይል እንደሚያስፈልግ ኢየሱስ ስለሚያውቅ የሚረዳ፣ የሚያጽናና እና የሚመራ ይልን እንደሚልክላቸው ቃል ገባላቸው። በመጨረሻም የእናንተ ፍርያማነት የሚወሰነው ከእኔ ጋር ባላችሁ ቁርኝት ላይ ነው አላቸው። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው እውነተኛ ወኪሎችህ ነን ካላችሁኝ ትዕዛዜን ጠብቁ፣ ትዕዛዜን ለመጠበቅ በመንፈስ ቅዱስ ዕለት ዕለት ተሞሉ፣ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር በመሆን ዕለት ተዕለት ኑሩ። ይህንን ብታደርጉ በእርግጥም በእኔ ውስጥ ትኖራላችሁ ቃሌም በእናንተ ውስጥ ይኖራል። ያኔ በስሜ የምትለምኑትን ነገር ሁሉ ታገኛላችሁ። ኢየሱስ ግን የምንለምነውን ነገር ሁሉ ሊሰጠን ነው ቃል የገባልን ወይስ በስሙ መጸለይ ማለት እንደ እውነተኛ ወኪሎች መጸለይ ማለት ነው? የዞንዶርቫን ባይብል ኮሜንቴሪ ስለዚህ ያለውን ሀሳብ ስገልጽ “እርሱ (ኢየሱስ) የሚመልሳቸው ጸሎቶች እርሱ ከሚፈልገው ባህርይ እና አለማ ጋር የሚጣጣሙትን ብቻ ነው” በማለት ገልጸዋል።" እርግጥ ነው ኢየሱስ እያለ የነበረው እንደ እውነተኛ ወኪሎች ብትጸልዩ የሚትጸልዩትን ነገር ታገኛላችሁ። ምክንያቱም እውነተኛ ወኪል የሚጸልየው እንደራሱ ፍላጎት ሳይሆን የወከለውን ሰው ፍላጎት በሚያሟላ መንገድ ስለሆነ እንደ እግዚአብሔር ፍላጎት ብንጸልይ ደግሞ ጸሎታችን ምላሽን የማግኘቱ እውነታ የሚያጠራጥር አይሆንም።
ስለዚህ በዘመናችን እንደ ጸሎት ማሳረግያ የምንጠቀመውን “በስምህ ጸለይን”ን ትተን እውነተኛ የቃሉን ትርጉም እንያዝ:: ኢየሱስ እውነተኛ ወኪሎቹ እንሆን ዘንደ ጠርቶናል። “በኢየሱስ ስም ለምኑ የሚለው ሀረግ መለኮታዊ ይልን ማዘዥያ የሚውል ምታታዊ ቀመር አይደለም። እንዲሁም ጠንቋዬች ጥንቆላቸውን እንደ ምያከናዉኑበት የመነባንብ ቀመር ይህንንም እንዲመለከቱት ኢየሱስ አልፈለገም። በጸሎታችን የራሳችንን የልብ መሻት ሳይሆን እርሱ አላማውን እና ፍቃዱን በእኛ እንዲፈጽም እንጠራዋለን። ወልድ አብን ያከብር ዘንድ ለእንዲህ አይነቱ ጸሎት ምላሽ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል።" ምላሽን የሚያገኘው የእውነተኛ ወኪል ጸሎት ነው። እውነተኛ ወኪልነታችን የሚታወቀው ለእርሱ በመታዘዛች ነው። ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ የምንችለው በመንፈስ ቅዱስ በየዕለቱ በመሞላት ነው። ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት ለእግዚአብሔር እራሳችን ማዘጋጀት ይጠበቅብናል። በመንፈስ ቅዱስ እለት እለት ስንሞላ እኛ በእርሱ ውስጥ መኖር እንችላለን ቃሉም በውስጣችን ይኖራል። እርሱም በስሙ የምንለምነውን (እንደ እውነተኛ ወኪሎች የምንጠይቀውን) ነገር ሁሉ ይሰጠናል። ምክንያቱም እውነተኛ ወኪሎች የሚጸልዩት እንደ የእግዚአብሔር ፍቃድ ስለሆነ ጸሎታቻው ሁሉ ምላሽ እንደሚያገኝ ቃል ገብቷል። ይህ ነው እንግዲህ በስሙ መጸለይ የሚለው ቃል ትክክለኛ ትርጉም። ለዛሬው በዚህ አበቃሁ።
Thomas L. Constable, Notes on John, 2005. 217
ወኪል፡ (ሎች)፤ የተወከለ፡ የታመነ፡ እሙን፤ ተጠሪ፡ ቶፋ፡ የሥራ፡ የነገር።
ዝኒ ከማሁ, 217
Keener, Craig S., IVP Bible Background Commentary: New Testament , (Downer’s Grove, IL: InterVarsity Press) 1997.
ተክለ ወልድ፣ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃለት (አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣አዲስ አበባ፣ 1970) ገጾ 1132
ዝኒ ከማሁ ገጽ 1132
ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሐፈ፡ ስዋሰው፡ ወግስ፡ ወመዝገበ፡ ቃላት፡ ሐዲስ፤1925 ዓም፣ ገጽ 388
ዝኒ ከማሁ 217 በቅንፍ ያለው የራሴ ነው
Bruce, Barton B.; Fackler, Mark; Taylor, Linda K.; Veerman, David R.; Osborne, Grant; Comfort, Philip, Life Application Concise New Testament Commentary, Scripture Press Publications, Inc. Licensed by Victor Books. Database ©2003 WORDsearch Corp
ባህርይ የማንነት መገለጫ ነው። እውነተኛ ወኪሎች የሚመስሉት፤ ነገሮችን የሚከውኑት እንደ ወካያቸው። ኢየሱስም የሚትወዱኝ ከሆነ ትዕዛዜን ጠብቁ ብሏል።ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሕይወት የተወሰነ የአኗር ዘይቤን፤ የተወሰነ ባህርን ማየት ፈልጓል። መታዘዝ እና የእርሱ መሆን፤ እርሱን መውደድ የማይነጣተሉ ነገሮች ናቸው። የሕይወታቸው አለማ እና መድረሻ የእርሱ ግብ እና መድረሻ ነው። ስለዚህም እርሱ ከሚፈልገው አለማ እና ባህር ጋር ለሚጣጣሙ ሰዎች እግዚአብሔር ለጸሎታቸው ምላሽ ልሰጥ የግድ ነው።
Kenneth L. Barker & John Kohlenberger III, ZONDERVAN NIV BIBLE COMMENTARY, (Grand Rapids, Michigan: Zondervan Publishing House), 1994. በቅንፍ ውስጥ ያለውን እኔ ነኝ የጨመርኩት
Apologists Bible Commentary John 14: 14-16 ,http://www.forananswer.org/, Nov8,2008

Comments
Post a Comment