“እውነት የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እና የመሃመድ አምላክ” አንድ ናቸው?

“እውነት የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እና የመሃመድ አምላክ” አንድ ናቸው?

በተካልኝ ዱጉማ (Duguma@gmail.com)
ከጥቅት አመታት ጀምሮ የአለም ሁሉ ትኩረት የሆነው የሙስልሞች አንቅስቃሴ ነው። በአለማችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖማያዊ እና ይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ይህ የይማኖት ከፍተኛ ተጽእኖ ማምጣቱ ሀገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው እውነት ነው። ለዚህም ይመስላል በአሁን ሰዓት ሙስልሞችን በወንጌል የመድረስ ራዕይ የሰነቁ ሰዎችን በብዛት መመልከት የጀመሪነው። ይህ ደግሞ እሰየው የሚያስብል ነው። ምንም እንኳ አንዳንድ የሚያስፈሩኝ ነገሮች ብኖሩትም። ድሮ ድሮ የሙስልሞች ቁጥር እጅግ አናሳ ከመሆኑ የተነሳ የምንመለከታቸው አልፎ አልፎ ብቻ ነበር። ነገር ግን አሁን ቁጥራቸቸው በዝቶ እለልፍ አላፍ ሆነዋል። እንዲያውም በአንድ አንድ ቦታዎች …። ዛሬ የሙስልሞችን እድገት ወይም በሀገራችን በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያስከተሉትን ተጽእኖ ለመዳሰስ ሰይሆን እንደ ቀልድ ብዙ ግዜ ስለው የነበረ ነገር ግን ድንገት አንድ ቀን በደንብ እንዳጤነው እና እንዳስብበት ስለተገደድኩት አንድ ነገር ላካፈልችሁ ስለፈለግኩ ነው። እንደ ቀልድ ብዙ ጌዜ ሰዎች “የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እና የመሃመድ አምላክ ይባረክ” ስሉ አደምጫለሁ የነገሩ ምንነት ጠንቅቄ ባላውቅም በቀልዳቸውም ተሳተትፌ የማውቅ ይመስለኛል። ይህ ቀልድ አዘል ንግግር መሰረት ያደረገው በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠው የኢየሱስ ክርስቶስ አባትን (እግዚአብሔር አብ) እና በቁራን የተገለጠው የመሃመድ አምላክ (አላህ) አንድ ናቸው በሚል እሳቤ ለይ ነው። ይህን እንደ ቀልድ ስመለከተው የነበረውን ሀሳብ በጥንቃቄ እንዳስብበት ያደረገኝ በክፍል ውስጥ የገጠመኝ ነገር ነው። cultural Anthropology አስተማሪያችን ትምህርቱን ይበልጥ በየእለት ህይወታችን ተግባራዊ እንዲሆን በመፈለግ ይመስላል ተጋባዥ አስተማሪን ይጋበዘለን። እኛም ደስ ብሎን ክፍለ ግዜውን እንከታተላለን። የዚያ እለት ተጋባዥ አስተማሪው በሙስልም ሚንስትሪ የሚያገለግል በመሆኑ እንዴት ሙስልሞችን በወንጌል መድረስ እንደሚቻል ከዚህ በፊት አስቤበት የማለውቀውን የአውዳዊነትን መንገድ ገለጸ። ነገሩ የሚያስደነግጥ፤ ያነሳቸው ሀሳቦች ከተለመደው መንገድ የወጡ በሆናቸው እናም እሰየው የሚያስብል፤ ለዘመናት የተዘነጉት ሙስልሞችን በወንጌል ለመድረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ በመሆኑ እንዲሁም በአሁን ሰዓት የአለማችን እና የሀገራችን ትልቅ ስጋት እየሆነ የመጣውን የእስልምና ይማኖት እድገትን የበኩሉን መፊቴሄ ለመስጠት የተነሳ በመሆኑ የተደባለቀ ስሜት ፈጠረብኝ። ነገር ግን ያነሳቸው ሃሳቦች በጣም ስላስፈሩኝ በጥንቃቄ ለማሰብ ተገደድኩኝ።
በዚህ ጽሑፌም የሚዳስሰው በአሁን ሰዓት ለሙስልሞች ወንጌልን ለመመስከር ውጤታማ የሆነው አውዳዊነት ዬትኛው ነው? የሚለውን ሳይሆን ዬትኛውም በእስልምና ዙርያ የሚደረግ ማንኛውም አውዳዊነት ስለምነካካቸው ወይም ልያትታቸው ስለምገቡ ሀሳቦች እና ቃላት ምንነት ነው። በመጀመሪያ አላህ የሚለው ስምን በመጸሐፍ ቅዱስ ላይ ለተገለጠው አምላክ መጠቀም አግባብነት እንዳለው የቃሉን ሥረወ ግንድ ጥናትን አሳያለሁ። ሁለተኛ በመጸሐፍ ቅዱስ የተገለጠው አምላክ እና በቁራን የተገለጠው አምላክ አንድ አለመሆናቸውን አሳያለሁ። በመጨረሻ በርዕሰ አንቀጹ ላይ ለተጠየቀው ጥያቄ ምላሽ በሁለት መንገድ በመግለጽ አጠናቅቃሉ።
“አላህ የሚለው ቃል ከመሃመድ መምጣት በፊት በአረብ ምድር ይኖሩ የነበሩ ሰዎች አማልከቶቻቸውን ለመጥራት ይጠቀሙበት እንደ ነበር የሚያሳይ ታርካዊ፣ ስነ-ጽሑፋዊ እና ስነ-ቅርሳዊ ማስረጃዎች አሉ።” እስልምና በአረብ ውስጥ ከመጀመሩ በፊት “በአረብ ውስጥ ጸሐይ እንደ ሴት አማልክት ጨረቃ ድግሞ እንደ ወንድ አማለክ ይታይ ነበር። ወንድ አምላክ ሆነው ጨረቃ የተለያዩ መጠርያዎች ይጠራሉ። አላህ በአረብ ምድር ከነበሩት አማለክት መካከል አንዱ እና ከሁሉም በላይ ነበር። … በመሃመድ ግዜ አንድ አላህን አምላክነት በአረብ ውስጥ እየተስፋፋ መጥቶ የነበረበት ምክንያት አረቦች ከክርስትያኖች እና ከአይሁዶች ጋር ባላቸው ግንኙነት ተጽእኖ ወይም በኢ-አማንያን ጎሳዎች መካከል የራሳቸውን የጎሳ አማላክ አላህ በማለት መጥራት በተነሳው አለማስማማት ልሆን ይችላል። ምንም እንኳ አላህ ከሁሉ በላይ እና ፈጣሪ መሆኑ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ብኖረውም በኢ-አማንያን ዘንድ ግን ይህ የተዘነጋ እውነት ነበር።” እንዲሁም “ከእስልምና በፊት በአረብ ውስጥ በሚኖሩ ኢ-አማንያን ዘንድ አላህ ብቸኛው መለኮት ሳይሆን ረዳቶች፣ አጋሮች፣ ወንድ እና ሴት ልጆች ያሉት ስሆን ይህንን ሀሳብ እስልምና ግን በጣም ይቃወመዋል።” “ከእስልምና መምጣት በፉት በመካ ውስጥ አላህ የሚለው ስም እንድ ፈጣር እና ከሁሉ በላይ የሆነን አምላክን ያመለክት ነበር” ። ይህ በመካ ውስጥ አንድ አላህ ብቻ ይመለካል ወደ ሚል መደምደሚያ ግን አያደርሰንም። ምክንያቱም “ከእስልምና በፈት የነበሩት አረቦች አላህ እነርሱ ትንንሽ አማልክት የሚሏቸው ረዳቶችን እና አጋዦች ነበሩት።” ይህ እንግድ አላህ የሚለው ቃል ከእስልምና መወለድ በፊት ሌሎች አማለከት መኖራቸውን ሳይቃወም ነገር ግን አንድ ከሁሉ በላይ የሆነ መለኮት የሚያመለክት ቃል እንደሆነ እንመለከታለን።
እንዲሁም አላህ የሚለው ቃል ሥረወ ግንድ የጥንት የሴም ነገዶች ቋንቋ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። “አላህ የሚለው ቃል ምንጩ መለኮትን ከሚያሳያ ከጥንት የሴም ነገዶች ቋንቋ ነው። ከነአናዊያን መለኮትን ‘ኤል’ ስሉ ሜሴፖታሜያዊያን ‘ኢሉ’ ይላሉ። የመጽሐፍ ቅዱስ የመለኮት ስያሜ ‘ኤሌሄም’ ነው።” እኔ በዚህ ስፍራ ላይ ማሳየት የፈለግኩት አላህ የሚለው ስም ከእስልምና ይማኖት መወለድ በፊት አማልክትን ለማመልከት በአረብ ውስጥ ይጠቀሙበት የነበረ መሆኑን እና አላህ የሚለው ቃል ሥረወ ግንድ በሴም ነገዶች ቋንቋ ውስጥ መሃመድ ከመምጣቱ በፊት መለኮትን ለማመልከት ይጠቀሙበት የነበረ መሆኑን ነው። በዚህ ምክንያት አላህ የሚለውን ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለተገለጠው አምላክ መጠቀም በራሱ ምንም ችግር አይኖረውም።
ሌላኛው በጥንቃቄ ልንመለከተው የሚገባው ነገር አላህ በሚለው የአረብኛ የመለኮት መጠርያና እና ኤሎሄም በሚለው የእብራይስጥ የመለኮት መጠርያ መካከል ያለውን ዝምንድናን ነው። አንዳንድ ሙስልሞች ይህንን መመሳሰል አይቀበሉ። ምክንያቱም ኤሎሄም ተውላጠ ስም ሳይሆን ለአማልክት የሚሰጥ አጠቃላይ ስም ነው ይላሉ። ኤሎሄም በመጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉን ቻይ የሆነውን በመጸሐፍ ቅዱስ የተገለጠውን እግዚአብሔር ብቻ ሳይሆንለ ለጣኦታት አማልክትም ስያሜ ሆኖ እናገኛዋለን። (ዘፍ 1፡1፣ መዝ 69፡5) ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች አላህ የሚለው ስም በተውላጠ ስምነት እንጂ እንደ ኤሌሄም ለአማልክት መጠርያነት የተሰጠ አይደለም ይላሉ ። ስለዚህ ሁለቱ ስያሜዎች ተለዋዋጭ እና ተስተካካይ አይደሉም በማለት ይከራከራሉ። “አላህ የሚለው ስም በጣም ጠቃም የሆነ የአማላክ ስም ነው። ከኤሎሄም ይልቅ ከያሔዌ ከሚለው የእግዚአብሔር ስም ጋር ይተካከላል ይላሉ። “አላህ” ለአማልክት የተሰጠ ስም ሳይሆን ተወላጠ ስም ነው። የተገለጠው አምላክ መጠሪያ ስሙ ነው ይላሉ። ሙስልሞች አላህ የሚለው ስም ለአማልክት የተሰጠ ስም ነው የሚለውን አስተምህሮ ይህ ቃል ልዩ እና ከሌላ ቃል በውርስ ልመጣ አይችልም በማለት ይቃወሙታል።” ነገር ግን Timothy C. Tennent የተባሉ ምሁር አላህ ኤሎሄም ጋር የሚያመሳስለውን አራት ዋና የሚባሉ ነጥቦችን አስቀምጠዋል “
1. ግልጽ የሆነ የቃሉ የሥረወ ግንድ በአላህ በሚለው በአረብኛ ቃል እና ኤሌሄም በሚለው የዕብራይስጥ ቃል መካከል መመሳሰል መኖሩን ያሳያል።
2. በአረብ አከባቢ በሚኖሩ ሰዎች ከእስልምና በፊት አላህ የሚለውን ቃል አንድ አምላክ በሆነ ሰዎች መካከል ለአንድ ሉአላዊ ለሆነ አምላክ ይጠቀሙበት እንደ ነበር ብዙ ታርካዊ እና ስነ- ቅርሳዊ ማስረጃዎች አሉ።
3. በአይሁዳዊያንም ይሁን በክርስትያኖች መጸሐፍት ትርጉም ውስጥ “አላህ” ከጥንት ጀምሮ እስዛሬ ድረስ እግዚአብሔርን ስምነት ስተረጎም ቆይቷል።
4. “አላህ” የሚለው ስም ሰፋ ያለ ትርጉም ያለውን የአምላክ ስምን ለመተርጎ ተጠቅሙበታል እንጂ ግለዊ፣ ለሙሴ የተገለጠውን የቃል ኪዳን ስም የሆነውን ያህዌን ለመተርጎም አልተጠቀሙበትም። አይሁዳዊያን እኛ አምላክ የሚለውን ቃል ለቃል ክዳኑ አምላክ እና ለሀሰተኛ አማልክት እንደምንጠቀምበት ሁሉ እነርሱም ተጠቅመውበታል። ነገር ግን ሙስልሞች አላህን የሚለውን ስም ለብቸኛው እና እውነተኛው አምላክ እንጂ ለሌሎች አማለክት አይጠቀሙበተም።”
“ኤሎሄም የምለው ቃል “ያል” የሚል ትርጓሜ አለው። ይህ ቃል በብዙ ቁጥር በመገለጽ አክብሮትነ ወይም “ሁሉን ቻይትን” እንደሚያሳይ ማሰቡ ትክክል ነው። ይህ ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለተገለጠው አምላክ መጠሪያነት (በስምነት) ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ መለኮትን ለሚያመለክቱ ሁሉ ስም ሆኖ ይታያል። (መዝሙር 82፡1፣ 1ሳሙኤል 28፡13)” እነዚህ ከላይ የተመለከትናቸው በአላህ እና በኤሎሄም በምለው የአምላክ ስም መካከል ትልልቅ መቀራረብ መኖሩን ያሳያሉ። ስለዚህም በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠው ኤሌሄም የሚለው የእግዚአብሔር ስም አላህ ከሚለውን ስም ጋር ተለዋዋጭ እና ተስተካካይ ትርጓሜው ይሆናል ማለት ነው። ሁለቱም ስሞች የሚያገለግሉት እንደ ተውላጠ ስምነት ሳይሆን እንደ በጠቅላላ መልኮታዊ ባህር አላቸው ተብሎ ለሚታመን አማልክት ስምነት ነው። ሁለቱም የሚያሳዩት አንድ ሁሉን ቻይ ያል አምላከን እንጂ አንደ ያሕዌ የቃል ኪዳን አምላክ የሆነውን ለሙሴ የተገለጠውን የአንድ አምላክ መጠሪያ ስምነት አይደለም።
ወደ ሁለተኛው ሀሳብ እናምራ። በመጸሐፍ ቅዱስ የተገለጠው እግዚአብሔር (ተለዋጭ ስሙ አላህ) በቁራን ከተገለጠው ጋር አንድ ናቸውንን? ወይም በሌላ አባባል በዋናነት የዚህ ጥያቄ መሰረት ሙስልሞች የሚያመልኩት አምላክ እና ክርስትያኖች እና አይሁዶች የሚያመልኩት አምላክ አንድ ነውን? የሚል ነው። በአለማችን ላይ ሶስት አንድ አምላክን አምላኪ ይማኖቶች አሉ። እነርሱም ክርስትና፣ እስልምና እና የአይሁዳዊያን ይማኖቶች ናቸው። እነዚህ ይማኖቶች በአለማችን ላይ አንድ ሁሉን የሚገዛ እና የሁሉ ፈጣሪ የሆነ አምላክ እንዳለ ያምናሉ። ጥያቄው ሁሉም አንድ አምላክ እንዳለ የሚያምኑ ከሆነ አንዱ አንዱን ልክ አይደለህም ማለት ይችላልን? የሚል ነው። ስለዚህም አንዳንድ ሰዎች “ክርስትያኖችም ይሁን ሙስልሞች ስለ እርሱ (ሰለ ፈጣሪያቸው) ስያወሩ፣ በምንም ስም ይጥሩት የሚያወሩት ስለ አንዱ አምላክ ነው ይላሉ” ። Mideast & N. Africa Encyclopedia እንዲህ ይሃል “ማስተዋል የሚገባን ነገር እነደ ሙስልሞች አስተምህሮ አላህ የነብዩ መሃመድ አምላክ ብቻ አይደልም ነገር ግን የሙሴን እና የኢየሱስም አምላክ ጭምር እንጂ። ስለዚህ የአይሁዳዊያን እና የክርስትያኖች ቅዶሳት መጽሐፍት ከሚያመለክቱት ፣መለኮት ጋር አንድ ነው” ግን ይህ አረፍተነገር ልክ ነውን? በጭራሽ! የሁለቱም የይማኖታቸው ወይም የእምነታቸው መሰረት የሀሳብ ወይም የፍልስፍላ ቀመር ብሆን ኖሮ አንድ ሁሉን ፈጣር፣ ከሁሉ በላይ፤ ሁሉን የሚችል አማላክ አለ በማለታቸው የሚያመልኩተ አማላክ አንድ ነው ባልንም ነበር። ነገር ግን ክርስትያኖችም ይሁን ሙስልሞች እንድሁ ተጨባጭ ያለሆ ምናባዊ የሐሳብ ቀመር የሆነ አምላክን አያመልኩም። ነገር ግን እነርሱ ይህ አምላክ እራሱን ገለጠበት ብለው የሚያምኑበት የእርሱን ማንነት የሚገልጽ መጽሐፍት አሏቸው። ስለዚህ ጥያቄው በቁራን ላይ የተገለጠው “አምላክ” እና በመጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠው አምላክ አንድ ነው ወይ? የሚል ይሆናል።
እርግጥ ነው በመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ እና በቁራኑ “አምላክ” መካከል መመሳሰል መኖሩን መካድ አይቻለም። ነገር ግን ሁሉት አንድ ናቸውን? ለምለው ጥያቄ መልሱ አንድ አይደሉም ነው። እስልምናን እና ክርስትናን አንድ የሚያደረጋቸው ሁለቱም “በአንድ አምላክ” ማመናቸው ነው። ነገር ግን ስለዚህ አምላክ ባህርያት እና ድርግት ስናገሩ የመመሳሰል እና የመላያት ነገርን ማስተዋል ይቻላል። ስለዚህ ነገር የቁራን እንዲህ ይላል “ እኛ ለእኛ በተገለጠው እና ለእናንተ በተገለጠው እናምናለን። የእኛ እና የእናንተ አምላክ አንድ ነው” ። (ሱራ 29፡46) ይላል። ይህ ጥቅስ ሙስልሞች የሚያመልኩት አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተገለጠው አምላክ ጋር አንድ እንደሆነ እንደሚያምኑ የሚያሳይ ይመስላል። ነገር ግን በክርትያኖች መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙትን ከቁራን ሀሳቦች ጋር በአንድ አንድ ቦታዎች የማይመሳሰሉበትን ምክንያት እንዲህ ይገልጹታል “የክርስትና ወይም የአይሁዳዊያን መጽሐፍት ሀሳብ ከቁራን ሀሳብ በሚቃረንበት ቦታ ሁሉ ይህ ሆን ተብሎ ወይም መጽሐፍቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ ስተላለፍ የመጣ ስህተት በኢ-እስላማዊ መጽሐፍት ውስጥ መኖሩን ሙስልሞች ያምናሉ” ስለዚህ ምንም አንኳ አንድ አምላክ እንዳለን ቢያስቡም ትክክለኛው አምልክ በእነርሱ ቁራን የተገለጠው እንጂ በእኛ፣ አሁን በእጃች ባለው መጽሐፍ ላይ የተገለጠው አምላክ እንዳልሆነ ያምናሉ ማለት ነው። ዛሬ በዬትኛው መጽሐፍ ትክክለኛውን አምላክ እንደተገለጠ በዝህ መጽሐፍ ለማሳየት አልሞክርም ነገር ግን የእኔ ነጥብ የሆነው ሁለቱ መጽሐፍት የሚያሳዩት “አምልክ” ልዩነት ያለው መሆኑን ነው።

ስለዚህ ወደ በርዕሰ አንቀጹ ላይ ለተገለጠው ጥየቄ ምላሽ እንስጥ። እውን “የኢየሱስ አባት እና የመሃመድ አባት አንድ ናቸውን?” የእኔ መልስ አይደሉም እና ናቸው ነው። አይደሉም የምልበት ምክንያት ሁለቱም ይማኖቶች አምላካችን የማወቅያ መንገዳቸው የተገለጠው በመጽሐፋቶቻቸው እስከሆነ ድረስ በእነዚህ መጽሐፍት የተገለጠው አምላክ ምንም እንኳ መመሳሰል ብኖረውም ልዩነት ስላለው አንድ አይደሉም ልል ተገድጃለሁ። ሁለት ምሳሌዎች ልስጥ። ሁለቱም ይማኖቶች አማላካቸው ሁሉን ቻይ እንደሆ ይነገራሉ። ነገር ግን ሁሉን ቻይነቱን ሁለቱም የሚገልጹበት መንገድ ይለያያል። የመጽሐፍ ቅደሱ አምላክ ያልነቱ በጥንካሬው ብቻ ሳይሆን በድካም ውስጥም እንደሚገልጥ በአዲስ ኪዳን ውስጥ እንመለከታለን። ለምሳሌ ሐዋሪያው ጰውሎስ እግዚአብሔር እንዴት ይላት እና ስልጣናትን እንደሸነፈ ስገልጥ እንድህ ነው ያለው “14እርሱ ያንን ይከሰንና ይቃወመን የነበረውን በሕግ ያለውን የዕዳ ጽሑፍ ደመሰሰው፤ በመስቀል ላይ ቸንክሮም ከእኛ አስወገደው። 15ኀይሎችንና ባለሥልጣኖችን በመስቀሉ ድል ነሥቶ ትጥቃቸውን ካስፈታ በኋላ ምርኮኞች ሆነው በይፋ እንዲታዩ አደረጋቸው።” (ቆላስያስ 2፡14-15) ይሀ እንግድ እግዚአብሔር ያልነት በድካም የተገለጠበት የመስቀሉ ስራ ነው። የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ያልነቱን ማንም የማይቋቋመውን ይሉን በመሳየት ብቻ ሳይሆን ተገለጠው ሰዎችን ከጢአት እስራት ለማሰለቀቅ እና የደንነት መንገድ ለማዘጋጀት ሞታቸውን በመስቀል ላይ ሞቶ፣ እንደ ሰው የሰውን ድካም ደክሞ፣ መከራንን እና ስያቃይን ተቀብሏል። ይህንን ዓይነት አመለካከት ግን የእስልምና እምነት እንደማይቀበለው በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ሰዎች እንዲህ በማለት ይናገራሉ። “ይህ አይነቱ [መለኮት መከራን እና ስቃይን ይቀበላል የምል አመለካከት] የመለኮት ያልነት መረዳት በግልጽ በባህላዊው የእስልማ አስተምህሮ ውስጥ ያሌለ እና ምክንያታዊነት የሚጎለው ነው” ይላሉ።ይህ አመለካከት ግን በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠው አምላክ መለያ በሕርይው በመሆኑ ሁለቱን ልዩ ያደርጋቸዋል ሁለተኛው። ሌላኛው የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ከቁራኑ “አምላክ” የሚለየው ምሳሌ የክርስትያኖች የማንነት መለያ እና የደንነታቸው መሠረት የሆነው የስላሴ፤ የኢየሱስ አምላክነት፣ የትስብእት፣ የመስቀሉ የማዳን ሀይል እና የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የመነሳቱ አስተምህሮዎች ናቸው። ዛሬ በዚህ ጽሑፍ እነዚህን አስተምህሮዎች በጥልቀት ለመዳሰስ ሳይሆን የቁራን እነዚሀ ከላይ የዘረዘርኳቸውን አስተምህሮዎች ስለማያስተምር በሁለቱ መጽሐፍት በሚገልጡት አምላክ መካከል ልዩነት መኖሩን ለማሳየት ነው። ይህንን ያስረግጥልኝ ዘንድ አንድ በመጽሐፍ ቅዱስ አምላክ እና በቁራኑ አምላክ መካከል ያለውን ልዩነት እና መመሳሰል ላይ ሰፍ ጥናት ያደረጉ አንድ የእስልምና ምሁር የተነጋረውን ልጥቀስ “ስለ አሀዱ ስሉስ እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን አስተምህሮ ብትተው እኔ እና እናንተ የምናመልከው አንድ አምላክ ነው።” በእርግጥ ነውን? በጭራሽ! እነዚህ ተው፤ አትንኳቸው የተባሉትን አንኳር የመጸሐፍ ቅዱስ እውነቶች እና የክርስትና እምነት መሰረቶች ብንተዋቸው ምን ይቀርልናል? በመጽሐፍ ቅዱሱ አማላክ እና በቁራኑ “አምላክ” መካከል መመሳሰል ልኖር ይችላል ነገር ግን አንድ አይደሉም። ስለዚህም የኢየሱስ ክርስቶስ አባት በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠው አማላክ ከሆነና የመሃመድ አማለክ በቁራን የተገለጠው “አምላክ” ከሆነ ሁለቱ አንድ አይደሉም። የሚያመሳስላቸው በሕርያት አሏቸው እንጂ።
አንድ ናቸው ያልኩበት ምክንያት በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠው አምላክ የኢየሱስ አባት ለመሆኑ እንዲሁም የአለማት ፈጣር እና አስተዳዳር መሆኑን ምንም ጥርጥር የለውም። ስለዚህ መሃመድ ከብዙ ዘመናት በፊት የኖረ ሰው በመሆኑ ምክንያት ያ የኢየሱስ አባት የሆነው የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ የመሃመድ አምልክም ይሆናል ማለት ነው። እርሱ በዚህ አምላክ ይመን አይመን ባላውቅም ማለት ነው።

ጽሑፌን ለማጠቃለል ያህል በዚህ ጽሑፍ አላህ የሚለው ስም ከእስልምና በፊት በአረብ ሀገራት ውስጥ አንድ ሁሉን የሚችል፣ ከሁሉ በላይ የሆነ ፈጣሪ አምላክን ለማመልከት ይጠቀሙበት ስለ ነበር እና የቃሉ ሥረወ ግንድ ከመጽሐፍ ቅዱሱ ኤሌሄም ጋር አንድ ስለሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠውን አምላክ አላህ ብሎ መጥራት በራሱ ምንም ችግር እንደሌለው አሳይቻሉ። አላህ የሚለው ስም ለጣኦት ተስጥቷል የሚል ተቃዋም ካለ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠው ኤሎሄም የሚለውም ስምም ለጣኦት ተሰጥቶ ስለሚያውቅ ልዩነት የለውም እላለሁ። ሁለቱ ስሞች በተውላጠ ስምነት ሳይሆን መለኮትን ለማመለክት እስከ ተተጠቀሙ ድረስ ችግር አይኖረውም። ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠው አምላክ እና በቁራን የተገለጠው “አምላክ” አንድ ናቸው? ለሚለው ጥያቄ የእኔ ምላሽ አይደሉም የሚል ይሆናል። ይህ ግን በሁለቱ መካከል ምንም መመሳሰል አይኖረውም ማለት ግን አይደለም። ለዚህ ምላሽ መሰረት ያደረግሁት ሁለቱም ይማኖቶች በምናብ፣ በሀሳብ እና በፍልስፍና አንድ ፈጣር እንዳለ በማመን እምነታቸውን በዚህ መሰረት ላይ የጣሉ አይደሉም። ነገር ግን ሁለቱም ይማኖቶች አምላካቸው እራሱን ገልጦበታል የሚሉት መጽሐፍት አሏቸው። እነዚህ መጽሐፍት የሚያመለክቱት አምላክ በአንድ አንድ ቦታዎች ላይ መመሳሰል ብኖረውም አንድ አይነት ግን አይደለም።

በመጨረሻ እውነን “የኢየሱስ አባት እና የመሃመድ አምላክ” አንድ ናቸውን? ለምለው ጥየቄ ምላሼ አይደሉም እና ናቸው እንደሆነ ገልጫለሁ። አይደሉም ያልኩበት ምክንያት የጥያቄአችን እስቤ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠው አምላክ እና በቁራን ተገለጠው “አምላክ” ላይ ስለሚሆን፤ ሁለቱ ደግሞ ምንም እንኳ የሚያመሳስላቸው ነገር መኖሩ የሚካድ ባይሆንም ልዩነት ስላላቸው፤ ምላሼ አይደሉም ሆኗል። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ሁሉ ፈጣር እና አምላክ በመሆኑ ምክንያት መሃመድም ከዘመናት በፊት ይኖር የነበረ ሰው በመሆኑ የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ለእርሱም አምላክ ልሆን ችሏል።
ስለዚህ ዛሬ በዚህ ጽሑፍ ማስተላለፍ የሚፈልገው ነገር ወንጌልን ሰዎች በሚረዱበት መንገድ ለማስተላለፍ እነርሱ በምናገሩበት ቋንቋ፣ አስተሳሰብ፣ ባህል እና ወዘተ መናገሩ መልካም ሆኖ ሳለ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጠው አምላክን ከሌሎች አማለክት ጋር ማስተካከል ግን አግባብነት የለውም ባይ ነኝ። አላህ የሚለውን ስም ወንጌልን ለምንነግራቸው ሰውች አምላካችንን ለማመልከት መጠቀሙ አግባብነት ቢኖረውም በመጽሐፍ ቅዱሱ “አላህ” እና በቁራኑ “አላህ” መካከል ልዩነት እንዳለ ማሳየቱ ግን በጣም አስፈላግ ነው። ማንኛውም የአውዳዊነት ግብ ልሆን የምገባው ወንጌልን ለሰዎች በምረዱት መንገድ መልእክቱን ሳይቀይጡ ማስተላለፍ ነው። በባህላቸው ውስጥ የሚናገኘውን ጠቃም ዕሴት ወንጌል ለማድረስ እንደ ጥርጊያ መንገድ ወይም ድልድይ ልንጠቀምበት እንችላለን እንዲሁም ይገባል። ነገር ግን ልዩነቱን አጉልተን መሳያየት ከተሳነን ወደ ቅይጣዊነት እንገባለን። ስለዚህ ጥንቃቄ አናድርግ እላለሁ። ለዛሬ በዚሁ አበቃሁ።

Comments